TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
Язык сайта
Russian
English
Uzbek
Вход на сайт
Каталог
Каталог каналов и чатов
Поиск каналов
Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов
Рейтинг чатов
Рейтинг публикаций
Рейтинги брендов и персон
Аналитика
Поиск по публикациям
Мониторинг Telegram
©Legal details center© :የህግ ማብራሪያ ማዕከል©
13 Jan, 12:48
Открыть в Telegram
Поделиться
Пожаловаться
በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ተጠየቀ
***
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች ጠይቀዋል።
የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች፣ ከግብጽ መንግሥት ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብና የወርቅ ሥጦታ በመቀበል የግብጽን ጥቅም ለማስጠበቅ በሞከር ጥፋተኛ በተባሉት የቀድሞው የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ጠይቀዋል።
ሜኔንዴዝ ጥፋተኛ ከተባሉባቸው ክሶች መካከል፣ የኢትዮጵያና ግብጽ የሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ለመፍታት በሚደረገው ድርድር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሚና እንዲጫወት በመጠየቅ ያልተገባ ተጽዕኖ ለመፍጠር ሞክረዋል የሚል ይገኝበታል።
ክሱን ተከትሎ ሜኔንዴዝ የምክር ቤቱን መቀመጫቸውን መልቀቃቸው አስታውሶ ሲኤንኤን ዘግቧል። የፌደራሉ ፍርድ ቤት በሜኔንዴዝ ላይ የእስር ብይኑን ጥር 21 ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው የኒው ጀርሲው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የውጭ መንግሥት ፍላጎትን ለመፈጸም ሥልጣናቸውን መጠቀም፣ ጉቦ መቀበል፣ ማጭበርበር፣ ፍትሕን ማደናቀፍን ጨምሮ በ16 የወንጀል ድርጊቶች ተከሰው በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#Federalerhicsand anticorroption
================
=
609
0
1
1
×