የመንደር ውሎች በሕግ ፊት ተቀባይነታቸው ምን ያህል ነው❓ውል የሚጸናው ምን ሲሟላ ነው❓
አራት ነገር ካልተሟላ ውል አይጸናም ።
1ኛ• ፈቃድ (Consent) ነው። ተዋዋዩ ፈቃዱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ በማያሻማ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ምን ማለት ነው ይሄ፣ በመታለል/በማታለል የተፈጸመ ውል ዋጋ አይሰጠውም።
2ኛ• ተዋዋዮቹ በሕግ 'ችሎታ ያላቸው' መሆን አለባቸው። 'ችሎታ' የሕግ ትርጉሙ ሁለት ነው። የተዋዋዮች ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና የአእምሮ ጤና ነው።
3ኛ• የውሉ ዋና ጉዳይ በሕግ የሚፈጸም መሆን አለበት። ለምሳሌ ባዶ መሬት መሸጥ አይቻልም። ስለዚህ የባዶ መሬት ሽያጭ ውል ቢደረግም በፍርድ ቤት ውድቅ ነው።
4ኛ• የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ 2 ምስክሮች መኖራቸው፣ በውል አዋዋይ ፊት መረጋገጥ፣ ሕጉ ያስቀመጣቸው ዝርዝሮች ሟሟላት።
የመንደር ውል ሕጋዊ ነው❓
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣ ማለትም ቤትና መሬት በርካታ ሰዎች በመንደር ውል የሚሻሻጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ተግባሩን ስላደረጉት ግን ሕጋዊ አያሰኘውም። ይህ የመንደር ውል በሕግ ተቀባይነት የማይኖረው የሰነድ ማረጋገጥ ዋና ዓላማን የሚጥስ መሆኑ ነው ።
ሰነድ ለምን ይረጋገጣል? ባይረጋገጥስ ምን ችግር አለው ❓
አንደኛ በተዋዋዮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግዛት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሦስተኛ ወገን ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ሦስተኛ ወገን የሚባሉት እነማን ናቸው ያልን እንደሁ፣ ከገዥና ሻጭ ውጪ ያሉ የትኛውንም ወገኖችን ያካትታል። ለምሳሌ የመንግሥት አካል፣ የክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ባንክ፣ ለምሳሌ ሽያጩ ይፍረስልኝ የምትል/የሚል ሚስት/ባል . . . ወዘተ እነዚህ ሁሉ 3ኛ ወገን ይባላሉ።
ከእነዚህ አካላት አንዱ፣ እንበልና በመንደር ውል በተፈጸመ ንብረት ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ሙግቱን ያለምንም እሰጥ አገባ አሸነፉ ማለት ነው። በመንደር ውል ቤት የገዛ ሰው ቀለጠ ማለት ነው። በአጭሩ ውል የሚረጋገጥበት ዋንኛ ዓላማ ሦስተኛ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። "የመንደር ውል ችግሩም ይሄ ነው።
እርግጥ ውል በሰነዶች ሲረጋገጥ መንግሥት ቴምብር ያሳርፍበታል። ገቢ ያገኛል። ገዥና ሻጭ ሰነዱን ይዘው ክፍለ ከተማ ሲሄዱ የመንግሥት አካል ቀረጥ ይጥላል። ከዚያም ገቢ ይገኛል። ተዋዋዮች ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስለቀረቡ፣ ሕጋዊ አገልግሎት አግኝተው የስም ማዞርያ አሹራ ይከፍላሉ። ይህም ሌላ ገቢ ነው። ለዚህም ነው ውሉ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን ፎርም ስላሟላ እንደ ሕጋዊ ውል ተቆጥሮ ተፈጻሚነት የሚኖረው።
ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ግን ምን ማለት ነው❓
በአጭሩ ለምሳሌ ሻጭ ለገዢ ስም አላዞርልህም ቢል ፍርድ ቤት ከሶ በግዴታ ስም እንዲያዞር፣ ገዥ ላይ ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንዲያገኝ ይሆናል ማለት ነው። ይህን ዕድል ግን በመንደር ውሎች ላይ ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል።
በመንደር ውል የተሸጠ ንብረት እጣ ፈንታው ምንድነው❓
በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ ውል፣ ወይም በውል አዋዋዮች ፊት ያልተረጋገጠ የመንደር ውል እንደ ሕጋዊ ተቆጥሮ አፈጻጸም ሊቀርብበት አይችልም። በዚህ ላይ ምንም ብዥታ መኖር የለበትም። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆን አለበት፣ በሁለት ምስክሮች ፊት መሆን አለበት። በአዋዋይ ፊት መሆን አለበት።
ወደ ጥያቄው ውሉ በመንደር ቢደረግ እጣ ፈንታው ምንድነው የሚሆነው❓
እውነት ለመናገር በዚህ ረገድ ሕጉ የተረጋጋ አይደለም :: የአገሪቱ የመጨረሻ ፍርድ ቤት የሆነው ሰበርም ቢሆን ከውል አዋዋይ (ውልና ማስረጃ) ውጪ የተደረጉ የመንደር ውሎች ይፀናሉ ወይስ አይፀኑም በሚለው ላይ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ ሰጥቷል።
በአንድ በኩል፣ ሰዎች በመንደር ከተዋዋሉና ነገር ግን ፊርማቸውን ካልተካካዱ ውሉ በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ይጸናል ብሎ የወሰነበት ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቍ 21448)
በሌላ በኩል ደግሞ የመንደር ውል በውል አዋዋይ ፊት እስካልተመዘገበ ድረስ ሕግ ተቀባይነት አይኖረውም የሚል ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቁ 83674)
ይህ ማለት ውሉ የሚጸናው በእነሱ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ግን አይችልም። ምን ማለት ነው፣ አንድ ሰው ቤቱን በመንደር ውል ቢሸጥና ውል ለማፍረስ ፍርድ ቤት ቢሄድ ገዥ ገንዘቡን ለመክፈል ይገደዳል። ሻጭም ቤቱን ለመስጠት ይገደዳል። ሆኖም ግን፣ ለምሳሌ ባንክ በቤቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረው የመንደር ውሉ አይጸናበትም። ወይም ደግሞ ሻጭ ላይ ባለ ዕዳ የሆነ ሰው ዕዳዬ ቤቱ ተሸጦ ይከፈለኝ ቢል ቤቱ ተሸጧልና አይከፈልህም ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በመንደር ውል ስለተሸጠ። አደጋውም እዚህ ላይ ነው። ገዢው የመንደር ውሉን ይዞ "እኔ እኮ ይሄን ቤት ገዝቼዋለሁ" ብሎ ጥያቄ ያነሱ ሦስተኛ ወገኖችን ዝም ሊያሰኛቸው አይችልም። ስለዚህ ገዢ በመንደር ውል መፈራረሙ ወዶና ፈቅዶ በራሱ ላይ አደገኛ አደጋን ጋብዟል::
ተዋዋዮች የመንደር ውልን ለምን ተመራጭ ያደርጋሉ❓
አሁን አሁን የተለመደው አሰራር ገዥና ሻጭ ውል የሚፈጽሙት በሁለት ዙር ነው። መጀመሪያ በመንደር ውል ይፈጣጠሙና ነው ወደ ሁለተኛ ውል አዋዋይ ዘንድ የሚመጡት። ብዙውን ጊዜ አንድ ቤት ስንት እንደተሸጠ በትክክል የሚታወቀውም በመንደር ውል ላይ እንጂ በትክክለኛው ውል ላይ አይደለም።
ተዋዋዮች ወደ መንግሥት ተቋማት ሄደው የሚዋውሉት በ2ኛ ደረጃ ነው። ይህን ሲያደርጉም ብዙውን ጊዜ ዋጋ ቀንሰው ነው። ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ትክክለኛ ዋጋ ተናግረው የሚዋዋሉት። መንግሥት ቢቸግረው ተመን አውጥቶ ያስክፍላል። 6 በመቶ አሹራ ትከፍላለህ። የተዋዋልከው ከተመኑ ከፍ ካለ በተዋዋልከው ያስከፍላል። ዝቅ ካለ ደግሞ በተመኑ ያስከፍላል።
በሁለት ዓይነት ዋጋ መፈራረም የሚያመጣው አደጋ ስምምነት ሲፈርስ ነው። አንድ ሰው ለምሳሌ ውል ይፍረስልኝ ብሎ ፍርድ ቤት ሲሄድ ውል ይፈርሳል። ውል ሲፈርስ ደግሞ ወደነበረበት ነው የሚመለሰው። ሻጭ ገንዘብ ይመልሳል፣ ገዥ ንብረቱን ይመልሳል።
በአሥር ሚሊዮን ብር የተሸጠ ቤት ውልና ማስረጃ ባረጋገጠው ውል፣ ፍርድ ቤት ተሂዶ ውል ቢፈርስ ተዋዋዮቹ ዋጋ ዝቅ አድርገው ስለሚዋዋሉ [ለምሳሌ 6ሚሊዮን ብር] ሻጭ ገንዘብ መልስ ይባላል። ይህን ጊዜ እንዲመልስ የሚገደደው በውልና ማስረጃ በገዛበትን ገንዘብ ነው። ይህ ማለት ገዥ 4 ሚሊዮን ብር ከሰረ ማለት አይደል?
በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚደረጉ የሽያጭ ውሎች በጽሑፍ ብቻ ሳይሆን በአዋዋይ ወይም ፍርድ ቤት ፊት መከናወን ይገባቸዋል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ; የማረጋገጥ መስፈርት ውሉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት እንዲኖረው ብቻ መከናወን ያለበት ሳይሆን ውሉ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውጤት እንዲኖረውም ጭምር መከናወን ያለበት ነው፡፡
rel='nofollow'>Http://t.me/judgeoffed