ክርክር ተደርጎ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ በፍ/ብ/ስ/ስ ህግ ቁጥር 358 መሰረት ያቀረበችዉ መቃወሚያ ክርክር መኖሩን አታዉቅም ነበር ለማለት ጣልቃ ገብታ መከራከር ስትችል ከቅን ልቦና ዉጪ ዉጤቱን ጠብቃ ያቀረበችዉ አቤቱታ ነዉ የሚለዉን ለመወሰን በእርግጥም የመቃወም አመልካች ቀደም ሲል ክርክር ሲደረግ የነበረ መሆኑን ክርክሩም የእሷን መብት የሚመለከት መሆኑን ታዉቅ እንደነበር መረጋገጥ ያለበት ፍሬነገር ጉዳይ ነዉ።
በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ወገን ባልተሳተፈበት ክርክር ተድርጎ መብቱን የሚነካ ፍርድ መሰጠቱን ባወቀ ጊዜ ፍርዱን በመቃወም መብቱን ማስከበር እንደሚችል በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ 358 ላይ ተደንግጓል፡፡
ይሁንና ይህንን መብት በመጠቀም ረገድ ክርክሩ መኖሩን እያወቀ በቸልተኝነቱ ወይም በእሱ ጉድለት የክርክሩ ተካፋይ ሳይሆን የቀረ ወገን ከቅን ልቦና ዉጪ ጉዳዩን ለማጓተት የሚያቀርበዉ መቃወሚያ ተቀባይነት ሊኖረዉ እንዳማይገባ ሰበር ችሎቱ ገዥ ዉሳኔ የሰጠበት መሆኑ ይታወቃል(ሰበር መ/ቁ/56795፣40229፣93987 እና ሌሎች መሰል መዝገቦችን ይመለከታል)፡፡
ተከሳሽ ባልና ሚስት ሆነዉ አይነጋገሩም ወይም ክርክሩን አያዉቁም ተብሎ አይገመትም የሚል (መነሻ) ያለማስረጃ ሊገመት አይገባም።
👇👇👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips