"አገር በሕግና በሕግ አግባብ ብቻ እንድትመራ እንታገላለን"
የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ተብሎ የወጣውን መመሪያ አስመልክቶ ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ ላይ የእናት ፓርቲ መግለጫ።
እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ላይ ክስ የመሰረተው ሐምሌ 17 ቀን 2015 ሲሆን በቀን 29/2/2016 ችሎቱ ክሳችንን እንድናሻሽል ብይን በመስጠቱ ክሳችንን አሻሽለን አቅርበናል። ስለሆነም የክሱ ሂደት ምን እንደነበረና ምን እንደሚመስል በየደረጃው የነበሩ ክርክሮችን በተመለከተ በጥቅሉ በዚህ መግለጫ እናቀርባለን።
የክሱ ምንነት፦ የንብረት ግብር ማስተባበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አጥንቶ ያቀረበውና በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ አማካይነት ሚያዚያ 3 ቀን 2015 በተጻፈ ደብዳቤ ሸኝነት ለሁሉም የከተማው አስተዳደር መዋቅሮች የተላለፈው የንብረት ግብር መመሪያ ሕግን ባልተከተለ መንገድና የከተማ አስተዳደሩ ባልተሰጠው ስልጣን የወጣ መመሪያ በመሆኑ ፓርቲያችን የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብን በመወከል መመሪያው እንዲሻርልን ለፍርድ ቤቱ ክሳችንን አቅርበናል።
የክሱ አመሰራረት፦ እናት ፓርቲ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብት መከበር በሰላማዊ ፖለቲካ ለመታገል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገበ አገራዊ ፓርቲ ሲሆን በማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ ላይ በደል አጋጥሟል ብሎ ሲያስብ ፖለቲካውን በፖለቲካ ሂደት፤ ፍትሕ ማግኘት የሚገባውን ጉዳይ ደግሞ ወደ ፍርድ ቤት አቅርቦ የመከራከር ሕገ መንግስታዊ መብት እንዳለን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37 ን.አ. 2 በግልጽ ተደንግጓል። ስለሆነም ይህ ሕገወጥ የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ በዘፈቀደ የተጫነ በመሆኑና እናት ፓርቲም ለሕዝብና በሕዝብ የተቋቋመ ፓርቲ እንደመሆኑ ሕዝቡ ላይ የፍትህ በደል ሲደርስ ሕግ እንዲከበር ዜጎች መብታቸው እንዳይጣስ ተገቢውን ሰላማዊ ትግል የማድረግ ግዴታ ያለበት በመሆኑ የአዲስ አበባን ሕዝብ በመወከል የወጣው የንብረት ግብር መመሪያ የሕግ መሠረት የሌለውና በሕግ ሥልጣን ሳይሰጠው ያወጣው መመሪያ በፍርድ እንዲሰረዝ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት የቀረበ ክስ ነው።
ተጠሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እናት ፓርቲ ለመሠረተው ክስ ሶስት የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ ያቀረበ ሲሆን እነሱም 1ኛ ፓርቲው የከስ ምክንያት የለውም 2ኛ የቀረበው ክስ ፓርቲው መብትና ጥቅማቸው አረጋግጠው ያቀረቡት ክስ አይደለም 3ኛ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ሳይገባ ውድቅ ተደርጎ መዝገቡ ሊዘጋ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ ተጠሪ ላቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚከተለውን ብይን ሰጥቷል፦ የመጀመሪያውን መቃወሚያ በተመለከተ የከስ ምክንያት የለውም የሚለውን አስተዳደሩ ሚያዚያ 3 ቀን 2015 ያወጣው የንብረት ግብር የሕግ መሰረት የሌለውና መመሪያ እንዲያወጣ በሕግ ስልጣን ሳይሰጠው ያወጣው መመሪያ በፍርድ ሊሰረዝ ይገባል የሚል ሲሆን ይህ ደግሞ በአዋጁ መሰረት የክስ ምክንያት ያለው ስለሆነ በዚህ ጉዳይ የቀረበው መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ እንዳልተቀበለው ብይን ሰጥቷል።
በሁለተኛ ደረጃ የቀረበው መቃወሚያ ፓርቲው ያቀረበው ክስ መብትና ጥቅማቸውን አረጋግጠው ያቀረቡት ክስ አይደለም የሚል ሲሆን ፍርድ ቤቱም ፓርቲው ህዝብን መሠረት አድርጎ የተቋቋመ ፓርቲ በመሆኑ የህዝብ መብትን ጥቅም ለማስከበር እና ህግ ለማስከበር ክስ ለመመስረት መብትና ጥቅም ስላለው በዚህ ዙሪያ የቀረበውን መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም።
በሦስተኛ ደረጃ አስተዳደሩ ያቀረበው መቃወሚያ ፓርቲው ያቀረበው ክስ በይርጋ ሊታገድ ይገባል የሚል ሲሆን ፍርድ ቤቱም የአስተዳደር መመሪያ እንዲሰረዝ የሚቀርብ አቤቱታ በማንኛውም ጊዜ መቅረብ እንደሚችል በዚህ ጉዳይ ላይ የይርጋ ተፈጻሚነት የለውም በማለት የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ያቀረበውን ሶስቱንም መቃወሚያዎች ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ ወደ ፍሬ ጉዳይ ክርክር ታሻግሯል።
የክስ መስማትና የፍሬ ነገር ክርክር፦ ዋናው ክስ ሰኔ 5 ቀን 2016 በፍሬ ነገር ላይ ቀደም ብሎ የቀረበው የጽሑፍ መከራከሪያ ነጥባችንን በማጠናከር የቃል ክርክር አድርገናል። ተጠሪ የአዲስ አበባ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮም በኹለት አቃብያነ ሕግ ተወክሎ ቀደም ሲል በጽሑፍ ያቀረቡትን የመከራከሪያ መልስ በቃልም እየተጋገዙ ተከራክረዋል። ሦስቱ ዳኞችም በርካታ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የራሳቸውን ግንዛቤ ወስደዋል።
የፍርድ ቤቱ ፍርድና ውሳኔን በተመለከት፦ ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ እልባት ለመስጠት ጭብጦች ይዟል።
በዚሁ መሠረት በተጠሪ(የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ) ሚያዝያ 3 ቀን 2015 በተጻፈ ደብዳቤ ወደ ትግበራ እንዲገባ የተደረገውና በንብረት ክፍል ማስተባበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የተዘጋጀው የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ሰነድ መመሪያ መሆኑን፤ መመሪያውም በፌደራል ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1182/15 ውስጥ የተደነገገዉን የመመሪያ አወጣጥ መርሆችን በመከተል የወጣ አለመሆኑን፤ መመሪያው የወጣውም የንብረት ግብር አዋጅ ባልወጣበትና ተጠሪ መሥሪያ ቤት ስልጣን ሳይኖረው የወጣ መሆኑንና ይህ የንብረት ግብር ለማሻሻል በሚል የተደረገው ጥናት በእነዚህ ምክንያቶች ተከልሶ ሕጋዊነቱን የሚያጣ መሆኑን ችሎቱ ደምድሟል።
በመጨረሻም ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በደብዳቤ ቁጥር ፋ/ቢ2/64/2249 በፋይናንስ ቢሮ በኩል ወደ ተግባር እንዲለወጥ የተጻፈው የግብር ማሻሻያ ጥናት ሰነድ በፍርድ ቤቱ መመሪያ መሆኑ ስለተረጋገጠ በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1182/2013 አንቀጽ 56(2) መሠረት ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም ተብሎ መመሪያው እንዲሻር ፍርድ ቤቱ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ባስቻለው ችሎት በሙሉ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቷል።
ውሳኔው በተሰጠ የሰዓታት ልዩነት ተጠሪ የከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ በውሳኔው ላይ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እስከሚል አፈፃፀሙና በጉዳዩ ላይ ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት የዕግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት በቃለ መሃላ አስደግፎ አቤቱታ ያቀረበ በመሆኑ ክብርት ፕሬዝዳንቷም ለ15 ቀን አፈፃፀሙ እንዲሁም ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ የዕግድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
ይሁንና እስከ ዛሬ ጥር 26 ቀን ድረስ ቢሮው ያቀረበዉ ይግባኝ ባለመኖሩና የእግድ ትእዛዙ የጊዜ ገደብም ያበቃ በመሆኑ ፓርቲያችን የፍርድ አፈፃፀም ስልጣን ላለዉ የአፈፃፀም ፍርድ ቤት ፋይል ለመክፈት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትም ለ15 ቀናት የሰጡት የአፈፃፀምና ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ የእግድ ትዕዛዝ ቀነ ገደብ ያበቃ በመሆኑ ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው ዕለት ልንሰጥ ችለናል፡፡ (ሙሉዉን የፍርዱን ሂደትና ዉሳኔ በአጠቃላይ 30 ገፅ ማግኘት ለምትፈልጉ የምናደርሳችሁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡)
በማጠቃለያ እናት ፓርቲ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንደሚያደርግ ፓርቲ ይህ የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪ በሙሉ የአነባበት ግብር የሕግ አግባብ ተከትሎ እንዲሻር ያስደረገበት አድካሚ ጉዞ ለሕዝባችን ጥብቅና መቆሙን ከማሳየት ባሻገር አንደኛው የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴው አካል መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል። ፓርቲያችን በቀጣይም በሕዝባችን ላይ ከሕግ አግባብ ውጪ የሚጫኑበትን ሸክሞች ወደ ፍርድ ቤት እያቀረበና በሕግ እየሞገተ የሚያስወግድ መሆኑንና ለዚህም በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ይገልጻል።