ከ5 ሺህ በላይ ሰራተኞች ውላቸው እንዲቋረጥ መመሪያ ተሰጠ።
ጤና ሚኒስቴር በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ (USAID) ድጋፍ የተቀጠሩ ከ5 ሺህ በላይ ስራተኞችን ውል እንዲቋረጥ መመሪያ ሰጠ።
ጤና ሚኒስቴር ከአሜሪካ መንግሥት በሲዲሲ (CDC) ወይም ዩኤስኤይድ (USAID) አማካኝነት በተገኘ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጃንዋሪ 24 ,2025 ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ እንደደረሰው ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ተፈርሞ ለሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች የተሰራጨው ደብዳቤ " በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ የተቀጠሩ እና ተቋማችሁ ከCDC ወይም USAID ጋር በሚያደርገው ውል መሰረት የተቀጠሩ ሰራተኞችን በተመለከተ ስራ ላይ እንዲውል አሳስባለሁ " ይላል።
ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የደብዳቤውን #ትክክለኛነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡን ተጨማሪ ማብራሪያ በመላው ሃገሪቱ በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ አማካኝነት በኮንትራት እያገለገሉ ያሉ ሰራተኞች ቁጥር 5 ሺህ እንደሚሻገር ገልጸዋል።
ሚንስትሩ " ሰው እንዲዘጋጅ ነው እንጂ የአሜሪካ መንግሥትም ሃሳቡን ሊቀይር ይችላል የተቀየረ ነገር ካለ የሚቀጥል ይሆናል አሁን ባለው ሁኔታ ግን ድጋፉን ካቋረጠ ሌላ መፍትሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል " ብለዋል።
" ለዚህ ደግሞ ሰራተኞቻችን እንዲዘጋጁ ከመንግስት ጋርም ንግግር እየተደረገ ነው ያለው የመንግስት ሰራተኞች ስራውን እንዲያስቀጥሉ የCDC እና USAID ሰራተኞች ስራውን እንዲያቆሙ ተወስኗል " ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በዝርዝር ምን አሉ ?
" እኛን በዋናነት የሚመለከተን በጀቱ በቀጥታ በእኛ በኩል ስለሚመጣ የሲዲሲ ሰራተኞችን ነው ዩኤስኤይድ ግን ቅጥር የሚያከናውነው በራሱ በኩል ነው ውሉንም የሚያቋርጡት ራሳቸው ናቸው።
የአሜሪካ መንግሥት ሃሳቡን ቀይሮ ሌላ መረጃ የሚያስተላልፍ ከሆነ እኛም ሌላ መረጃ የምናስተላልፍ ይሆናል አሁን ባለው የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ግን ኮንትራታቸውን ማቋረጥ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ደብዳቤ አስተላልፈናል።
ከ5 ሺ በላይ ይሆናል ትክክለኛ ቁጥራቸውን ለማወቅ መረጃ የመሰብሰብ ስራ እየሰራን ነው ሁሉም በኮንትራት ናቸው ኮንትራታቸው በየአመቱ ይታደሳል ስራቸውም ከኤች አይ ቪ ጋር የተገናኙ ስለሆነ አብዛኞቹ የቆዩ ሰራተኞች ናቸው።
በጣም አስፈላጊ በመሆናቸው ነበር በዚህ ያህል በጀት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረው 15 እና 20 ዓመት የሞላቸውም አሉ ስራው ላይ ችግር ሊያመጣ ይችላል።
በአንድ ጊዜ ይሄን ያህል ሰው ከሴክተሩ ከተቀነሰ ችግር ሊፈጠር ይችላል ዋናው ነገር ግን ስራው እንዳይስተጓጎል ሃላፊነቱን ላለው የመንግስት ሰራተኛ እያስተላለፉ መሄድ ያስፈልጋል።
ቀላል ስራ አይደለም የሚጠብቀን የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን።
የመጨረሻ ውሳኔዎችን አልሰማንም ከአሜሪካ መንግሥት በየጊዜው የተለያዩ ውሳኔዎች እየተላለፈ ስለሆነ ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ ነው የሚባለው ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ተመሳሳይ ነገር ነው እያደረጉ ያሉት ከሁሉም ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅትም በቦርድ ደረጃ ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።
ሰራተኞችም እንዲያውቁ እኛም ጫናውን ለማሳወቅ እና መፍትሄው አብሮ ለመፈለግ እንዲቻል ለመንግሥትም አሳውቀናል ስራ እንዳይጎዳ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል።
በዚሁ ከቀጠለ ሌላም ከባባድ ውሳኔዎች ሊወሰን ይችላል የመድኃኒት ግዢ እና ሌሎችም ድጋፎች ሊቋረጡ ይችላሉ አይታወቅም እንዳይቋረጥ እና እንዲቀጥል እኛም እንደሃገር የምንችለውን ጫና እናደርጋለን።