የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አፈጻጸም
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2017 ግማሽ አመት አጠቃላይ የገቢ አፈጻጸሙ ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የ116 በመቶ ብልጫ ያለው ዕድገት አስመዘገበ፡፡
በአገልግሎቱ የስድስት ወር አፈጻጸ ላይ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር በተደረገው ውይይት አገልግሎቱ ይህንን ከፍተኛ ገቢ ሊያገኝ የቻለው ከተለያዩ የሎተሪ ሽያጭና ከዕድል ጨዋታዎች ፈቃድ ኮሚሽን ገቢ ነው፡፡
በዚሁ ውይይት እንደተገለጸው አገልግሎቱ በግማሽ በጀት አመቱ የተጣራ ትርፍ ከያዘው ዕቅድ 158 በመቶ በማሳካት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡
አገልግሎቱ በቀጣዩ ግማሽ በጀት አመት ስትራቴጂያዊ የዲጅታል ሎተሪን ተግባራዊ ከማድረግ በተጨማሪ የአገልግሎቱን አፈጻጸም ቀልጣፋ ለማድረግ ድርጅታዊ መዋቅርና የቢስነስ ሞዴሉን በተግባር ለማዋል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጸል፡፡