ወጣቱ 5,000,000 / አምስት ሚሊየን / ብር ተሸለመ!
ወጣት ሰለሞን ሐድጉ ይባላል ነዋሪነቱ በመቐለ ከተማ ሲሆን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሎተሪ የመሞከር ልምድ አለው፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ጫማውን ለማስጠረግ ቁጭ ባለበት ቦታ የሎተሪ አዟሪ የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ቲኬት እንዲገዛው ይሰጠዋል ወጣት ሰለሞን ስራ ፈላጊ ነውና በአጋጣሚ ኪሱ ላይ የነበረው መቶ ብር ብቻ በመሆኑ ለሊስትሮው የሚከፍልበትና ለሎተሪ ቲኬት መግዥያ በማብቃቃት በ50 ብር የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የግማሽ ዕጣ ቲኬት በመግዛት ቲኬቱን በኪሱ ያስቀምጣል ፡፡ የማይደርስ የለምና የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ መውጫው ቀን ደርሶ ከወጣ በ5ኛው ቀን አስደንጋጭ እና ለማመንም ቀናት የፈጀበት ክስተት ተፈጠረ ፡፡ ማውጫውን ደግሞ ደጋግሞ ስያስተያይ ከ2ኛው ዕጣ በግማሽ የገዛውን ቲኬት የ5,000,000 / አምስት ሚሊየን / ብር አሸናፊ መሆኑን ያያል ፡፡ ወጣት ሰለሞን አሁንም መቶ ፐርሰንት በሚባል ደረጃ አላመንኩም ነበር ይላል እራሴን ካረጋጋሁኝ በኋላ ወደ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መስሪያቤት በመሄድ የ5 ሚሊየን ብር ዕድለኛ መሆኔን አረጋገጥኩ ፈጣሪ ይመስገን አሁን ግን ከፍ ያለ ደስታ ላይ ነኝ በማለት በማያቋርጥና የደስታውን ማሳያ የሆነው ፈገግታው ላየ ሰው እውነትም የሎተሪ ዕድል የሚሰጠው ደስታ ከሌላው ደስታ በብዙ ይለያል ማለቱ አይቀርም ትክክልም ነው ፡፡ ወጣት ሰለሞን ሐድጉ ታድያ ይሄ ዳጎስ ያለውን ገንዘብ ምን ልታደርግበት ነው ተብሎ ሲጠየቅ በመቀሌ ከተማ ቤት እገዛበታለሁ በቀሪውም ገንዘብ አነስተኛ ንግድ በመጀመር ኑሮየን አሻሽልበታለሁ በማለት ገልጸዋል ፡፡