MADO NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


. Your go-to source for the latest, most reliable news from Ethiopia and beyond! Get real-time updates, breaking stories, and insightful coverage from trusted sources. Stay ahead, stay informed, and never miss a beat! 📲
📩 @Mado_Inbox

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


መልዕክቱ ይሰራጭ‼
#ScamAlert
✍ ኧረ! ይሄን የጥንቃቄ መልዕክት በአስቸኳይ ሼር አድርጉት
!

ብዙ ሰው እየተሸወደ ነው።
«የቴሌግራም ፕሪሚየም በነፃ ተቀብለዋል!» የሚል የአማርኛ ጽሑፍ ከስሩ ሊንክ ያለው እየተሰራጨ ነው።
ልብ በሉ! ሊንኩን ከተጫናችሁት አካውንታችሁ 100% ተጠልፏል።

በምታውቁት ሰው አካውንት ቢላክም፤ አውቆ ሳይሆን እርሱም ተበልቶ ነው።
ሊንኩን በፍፁም እንዳትከፍቱ።

ሳታውቁ በስህተት የከፈታችሁ ካላችሁ በአስቸኳይ ይህን አድርጉ።

መጀመሪያ ፕሮፋይላችሁ ላይ ወዳለው Settings ላይ ግቡ Devices የሚለውን ንኩት። በቀይ የተፃፈውን Terminat All Other Sessions የሚለውን ተጫኑና ከሁሉም አካውንታችሁ ሎግኢን ከተባለባቸው ዲቫይሶች ውጡ።  Ok በማለት 24 ሰአት ሳይቆይ አስወግዱት። 24 ሰዓት ከቆዬ ይህን ማድረግ ላትችሉ ትችላላችሁ። ምክንያቱም እነርሱ ይህን ስቴፕ ተከትለው እንደ ዋና ባለቤት ሆነው እናንተን ያባርሯችኋል። 

ብዙ ሰው እየተበላ ስለሆነ ሼር it.
አሁን ማነው የ 5000 ብር የቴሌግራም ፕሪሚየም በነፃ የሚሰጣችሁ?
በአቋራጭ ለመበልፀግ አትጣደፉ።

[ @MadoNews ]


ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ጥሪ ተደርጎለታል።
ዶክተር ደብረፂዮን ዛሬ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ጥሪ ተደርጎለት የነበረ ሲሆን ጌታቸው ረዳ ከስልጣን ካልወረደ አልመጣም ብሎ መቅረቱን ሰምተናል።

[ @MadoNews ]


ለጥንቃቄ ተጠቀሙበት

ምስላቸው እና ዝርዝራቸው ከላይ እና ከታች የተቀመጡ የተለያዩ የገበታ ጨው ምርቶች የብሔራዊ ደረጃ ምልክቱን የመጠቀም ፈቃድ ያላገኙና ጥራት እና ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆናቸው ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳስቧል።

📌1. ሊኑ የገበታ ጨው /LINU IODIZED SALT /፣

📌2. ታሪክ የገበታ ጨው /TARIK TABLE SALT /፣

📌3. SALT BAY፣

📌4. ሺማ አዮዳይዝድ ጨው /SHIMA IODIZED SALT/

📌5. እና ጂ.ኤም ኤዳይዝድ ጨው /G.M Iodized salt/ በሚባል የምርት ስም የሚጠሩ ናቸው።

[ @MadoNews ]


4 ኪሎ በ3 ቀናት ውስጥ 345 እግረኞች መቀጣታቸው ተሰምቷል

በአራት ኪሎ አደባባይ ክፍት በሆነው የእግረኞች መተላለፊያ ዋሻ (Under Pass) እግረኞች በትክክለኛው መንገድ በአግባቡ አልተጠቀሙም ያላቸውን 345 እግረኞች በገንዘብ ቅጣት እንደቀጣቸው የአዲስአበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

[ @MadoNews ]


ጌታቸው ረዳ ''90 በመቶ የህዝብ ድጋፍ አለኝ'' ሲሉ ተደምጠዋል

90 በመቶ ህዝብ ሰላምን ስለሚፈልግ  ይደግፈኛል” ብለዋል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በአዲስ አበባ ለመገናኛ ብዙሃን  በሰጡት  መግለጫ ፡፡

አቶ ጌታቸው ደጋፊዎችን በተመለከተ ወጣቱ ሰላምን ስለሚፈልግ 90በመቶ ህዝብ እኔን እና መስተዳድሬን ይፈልጋል ብለዋል፡፡

90 በመቶ  ህዝበ ሰላምን መረጋጋትን የተፈናቃይን መመለስ ስለሚፈልግ ይደግፈኛል ብለዋል፡፡

70 በመቶ ህዝብ ወጣት ነው ስንል ሽማግሌ አይደግፍም  ማለት አደልም ሰላም ወዳድ ሁሉ ግን ጊዜአዊ አስተደዳደሩን ይደግፈዋል ብለዋል፡፡

[ @MadoNews ]


ትግራይ ውስጥ ‘ከሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን ከሚሉ ወገኖች አንዱ የ #ኤርትራ መንግሥት ነው’ ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በ #አዲስ_አበባ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ “ትግራይ ውስጥ ከሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ፤ የኤርትራ መንግሥት አንደኛው እንደሆነ አውቃለሁ” ሲሉ ተናገሩ።

“የኤርትራ መንግሥት ከፌዴራል መንግሥት ጋር የመጀመሪያ ግጭት ውስጥ የገባው #ፕሪቶርያን ከተስማማን በኋላ ነው” ሲሉ የተለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ “ከኤርትራ መንግሥት ጋር ሰላም እንፍጠር ማለት ኤርትራ በትግራይ ላይ የፈጸመችውን ጭፍጨፋ እንካድ ማለት አይደለም” ብለዋል።

አቶ ጌታቸው፤ “ክልሉ ወደ ሌላ ጦርነት መግባት የለበትም። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፌዴራል መንግስቱ ውሳኔ አካል ነው። የፌዴራል መንግስቱ አግባብነት ያለው ሃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል” ሲሉ ተደምጠዋል።

[ @MadoNews ]


አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በቀነኒ ሞት ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት ቀረበ

አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረቡን ጠበቃው ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጿል።

ፖሊስ እስካሁን አሻራ ማንሳቱን፣ አስከሬኑን ወደ ሆስፒታል በመላክ፣ የአስከሬን ምርመራ ማድረጉን ገልጾ የሰው ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

“አሁን ፎቶግራፎችን ከመዝገቡ ጋር ለማያያዝ፣ የሰዎች ምስክርነት ለመስጠት እና የአስከሬን ምርመራው እስኪመጣ ድረስ ለማጣራት 14 ቀናት ያስፈልገኛል ብሏል።

የአንዱአለም ጠበቃ በበኩሉ የዋስ መብት ይሰጥ ብሎ ቢጠይቅም ፍርድ ቤት የአስክሬን ምርመራ እንስኪደርስ በማለት 13 ቀናት ድምፃዊው በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ወስኗል።

[ @MadoNews ]


የ104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ በደብረጺዮን ገ/ ሚካኤል አመራሮች ቁጥጥር ስር ዋለ

በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት በተመደቡ የመቐለ ከተማ አመራሮች አባላት ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

አመራሮቹ በሰራዊት ታጅበው ሬድዮ ጣቢያውን እንደተቆጣጠሩት ተነግሯል።

[ @MadoNews ]


ቴሌግራም ሙሉ በሙሉ ተመልሷል!


በኢትዮጵያ ቴሌግራም ተቋርጧል።

የቴሌግራም መተግበሪያ ላለፉት ደቂቃዎች አገልግሎቱ ተቋርጧል። እዚህ ሀገር ውስጥ ብቻ ወይስ ሌሎችም ሀገራት የሚለውን በማጣራት መረጃ የምንልክላችሁ ይሆናል።

እስከዛው አገልግሎቱን በVPN መጠቀም ይቻላል።

በዳታ ሙሉ በሙሉ ያለ VPN የማይሰራ ሲሆን አንዳንዶች በWiFi ያለ VPN እየሰራላቸው ይገኛል። አንዳንዶች በWiFiም ሆኖ ያለ VPN እየሰራላቸው አይደለም።

    [ @MadoNews ]


- ኃፍረት የማይታይባቸው ናቸው በጥቂት ግለሰቦች ጥቅም ሲባል የትግራይ ህዝብ መጎዳት የለበትም
የትግራይ ህዝብ ወደ ባሰ መከራ ለማስገባት ርብርብ ላይ ናቸው።

- ትግራይ ህዝብ ሰላም ነው የሚሻው ድጋሚ ጦርነት አይፈልግም። የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲቀባ ጠይቀዋል።

- ይህ ቡድን ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ቀን ከለሊት አየደወሉ ስልጣን የሚለምኑ ኃይል ነው።

[ @MadoNews ]


"አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል" በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች

ፓርቲዎቹ በጦር በመታገዝ የሚደረግ የስልጣን ንጥቂያ ይቁም ሲሉም ባወጡት መግለጫ ላይ አካተዋል።

📌የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ፣
📌ባይቶናና
📌 ዓረና ትግራይ በጋራ ባወጡት መግለጫ "የህወሓት ካድሬ ጄነራሎችና አጋሮቻቸው በህገወጥ መንገድ ስልጣን ለመንጠቅ እየሞከሩ ባሉበት ወቅት የክልሉ ሰላምና መረጋጋት ወደ ቀወስ ውስጥ ከተውታል ብለዋል።

👉የኤርትራን ጣልቃ ገብነት እና የአካባቢውን ሰላምና መረጋጋት የሚፃረሩ የውጭ አካላት ሚናን ለመግታት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ሲሉም ገልፀዋል።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ህገወጥ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መንግስታዊ መዋቅር ከታች እስከላይ በማፍረስ ክልሉ ወደ ከፍተኛ አለመረጋጋት አስገብተዋል ያሉ ሲሆን ይህ በግዴሌሽነት እየተፈፀመ ያለው የስልጣን ወረራ የተናጠል ተግባር ሳይሆን ከኤርትራ መንግስት ጋር በመቀናደት የተሰራ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

በዚህ መሰረትም አለም አቀፍ አካላትና ሁሉም የፕሪቶርያ ስምምነት ተዋናዮች በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ እንጠይቃለን ያሉ ሲሆን ተጨማሪ ትርምስ ለመከላከልና እስከፊ ክልላዊ ቀውስን ለመከላከል ሲበላል የህግ የበላይነት መከበር አለበት ሲሉ ተደምጠዋል።

[ @MadoNews ]


ጌታቸው ረዳ በትግራይ ወቅታዊ ጉዳይ ከ አሜሪካ እና አውሮፓ አምባሳደሮች ጋር መነጋገራቸውን አሳወቁ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ በትግራይ እያሽቆለቆለ የመጣውን ኹኔታ መቀልበስ በሚቻልበት ኹኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመንና አውሮፓ ኅብረት አምባሳደሮች ጋር ትናንት መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

ጌታቸው፣ ውይይቱ የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ባለድርሻዎች ዳግም በትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማድረግ ባለባቸው ጥረቶች ዙሪያ ጭምር እንደኾነ በኤክስ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

በትግራይ ዳግም ጦርነት ከተቀሰቀሰ፣ ሥውርና አፍራሽ ዓላማ ያላቸው በርካታ የቀጠናው ኃይሎች ሊገቡበት የሚችሉበት እድል እንዳለ ጌታቸው ጠቁመዋል።

[ @MadoNews ]


የተስፋ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ውሳኔ ተላለፈ

ኢትዮጵያ በዓሉን ደግፋ ድምጽ በሰጠችበት በዚህ ጉባኤ ላይ አሜሪካ ውሳኔውን ተቃውማለች
የተስፋ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ውሳኔ ተላለፈ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባካሄደው ውሳኔ የተስፋ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲበር ውሳኔ አስተላልፏል፡

የረቂቅ ውሳኔ ሀሳቡን ኦስትሪያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሞሮኮ፣ ፊጂ እና ሌሎችም ሀገራት ያቀረቡ ሲሆን ዓለም አቀፍ የተስፋ ቀን በየዓመቱ በፈረንጆቹ ሐምሌ 12 እንዲከበር በአንላጫ ድምጽ ተሰጥቶበታል፡፡

የተመድ አባል ሀገራት የውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 166 ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን ዕለቱ በ162 ሀገራት ድጋፍ ጸድቋል፡፡

በዚህ ውሳኔ ላይ አሜሪካ ሀሳቡን ተቃውማ ድምጽ የሰጠች ሲሆን ሕንድ ፣ ቱርክ፣ ፔሩ እና ፓራጓይ ደግሞ ድምጽ ተዓቅቦ ማድረጋቸውን ከተመድ ድረገጽ ላይ የወጣው ሪፖርት ያስረዳል፡፡

ዓለም አቀፍ የተስፋ ቀን በየዓመቱ ስለ ተስፋ እና እኩልነት የተለያዩ ስራዎችን በመስራት እንደሚከበርም ተገልጿል፡፡
ውሳኔው መጽደቁን ተከትሎ ሁሉም የተመድ ተቋማት እና ድርጅቶች ስለ ተስፋ በተለያዩ መንገዶች ጉዳያቸው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ራሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተስፋን መሰረት በማድረግ መመስረቱን ምን ጊዜም ለሰዎች ተስፋን መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

[ @MadoNews ]


የየካቲት ወር የሀገሪቷ  አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15 በመቶ መሆኑን አገልግሎቱ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባወጣው መረጃ መሰረት የየካቲት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15 በመቶ ደርሷል።

ይህ አሀዝ ከጥር ወር ጋር ሲነጻጸር የ0.5 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን፣ በየካቲት ወር ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት መካከል የምግብ ነክ እቃዎች የ14.6 በመቶ ድርሻ ሲይዙ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ደግሞ 15.6 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ተጠቁሟል ።

[ @MadoNews ]


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በመቐለ ከተማ በእነ ደብረጽዮን  ቡድን እየተደረገ ያለዉን የግዚያዊ አስተዳደር መንግስት በሀይል የማፍረስ እና ትግራይን የማውክ ድርጊት የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው።

[ @MadoNews ]


1 ሺህ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የአደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በዚህ ወቅት÷4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።

በዚህም ከዛሬ ጀምሮ በሳምንት 9 በረራዎችን በማድረግ ዜጎችን የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ዜጎቹን የመመለስ ተግባር የመንግሥት የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አካል መሆኑንም ቃል አቀባዩ አንስተዋል።

[ @MadoNews ]


ተፈጸመ

የወ/ሮ ቀነኒ አዱኛ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ መጋቢት 03 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በ9:00 ሰዓት ተፈጽሟል።

[ @MadoNews ]


በዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ አምስት ባለጸጎች ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስረዋል ተባለ

ባለጸጎቹ ከጥር ወር ጀምሮ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው ተገልጿል
በዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ አምስት ባለጸጎች ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስረዋል ተባለ። 
የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሕዳር ወር ላይ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ጥር ወር ላይ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ወዳጆቻቸው፣ የሀገራት መሪዎች እና ባለጸጎች በተገኙበት በይፋ በዓለ ሲመታቸው ተከብሯል።
በዚህ በዓል ላይ የተገኙ የዓለማችን ቀዳሚ ባለጸጎች በዝግጅቱ ላይ ከተገኙበት ቀን ጀምሮ ኪሳራ እያስመዘገቡ እንደሆነ ብሉምበርግ ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳድር ዋነኛ አካል የሆኑት ኢለን መስክ ብቻ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ብቻ የ148 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አስመዝግቧል።

የአልፋቤቱ ሰርጌይ ብሪን 22 ቢሊዮን ዶላር፣ የሜታ ኩባንያ ባለቤቱ ማርክ ዙከርበርግ አምስት ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ፈረንሳዊው የፋሺን ኢንዱስትሪ ባለቤት በርናርድ አርናልት ደግሞ አምስት ቢሊዮን ዶላር መክሰራቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ 17 ኩባንያዎች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የ1 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶባቸዋል ተብሏል።

ለባለጸጎቹ የገቢ መቀነስ ምክንያት ከተባሉት ውስጥ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳድር አዳዲስ እርምጃዎች፣ ከሀገራት ጋር የገቡበት የንግድ እና ቀረጥ ውሳኔዎች እና የተወሰኑት ባለጸጎች ከአስተዳድሩ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አድርገዋል መባሉ ዋነኞቹ እንደሆኑ ተገልጿል።

[ @MadoNews ]

Показано 19 последних публикаций.