በጌዲኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል እና የአብነት ትምህርት አገልግሎቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ምክክር ተከናወነ።
በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ የተመራ ልዑክ ከጌዲኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ እና ከሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደርጓል።
በዲላ ከተማ በተደረገው ውይይት ማኅበረ ቅዱሳን በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ብፁዕነታችው በውይይቱ ላይ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ማድረጉ እጅግ እንዳስደሰታቸው የተናገሩ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ በተጠናከረ ሁኔታ ለቤተ ክርስቲያን እና ለምዕመናን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም የአቅም ውስንነት አለበት ብለዋል።
ብፁዕነታቸው ጨምረው እንደተናገሩት ማኅበሩ አሁን በሀገረ ስብከቱ ሊያከናውናቸው ያሰባቸው ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
በዕለቱ ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ የተከናወኑ ተግባራትን ለልዑካኑ ያስጎበኙ ሲሆን ማኅበሩ በሀገረ ስብከቱ የመጀመርያ የሆነና በ2018 ዓ.ም ለሚያስገነባው የአብነት ትምህርት ቤት የሚሆን 450 ካሬ ሜትር ቦታ መዘጋጀቱን አረጋግጠዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የደቡብ ማእከላት ማስተባበርያ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ቀሲስ አሰፋ በበኩላቸው ብፁዕነታቸው ወደ ሀገረ ስብከቱ ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸው በተለይም በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉ ሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት እየዞሩ በመመልከት የተዘጉት እንዲከፈቱ አድርገዋል ብለዋል።