#Press_Conference
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እሁድ ከአርሰናል ጋር ከሚደረገው ጨዋታ አስቀድመው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
"እሁድ መሸነፍ የለብንም ቡድናችን በትናንቱ ጨዋታ በመጨረሻ 20 ደቂቃዎች እጅግ ተዳክሞ ነበር ሆኖም ይሄን ከዚህ የድካም ስሜት ልናገገም ይገባል ።"
"ይሄንን ማድረግ ካልቻልን ግን እሁድ በከባድ ሁኔታ የምንቀጣ ይሆናል ባሉን ተጨዋቾች ጨዋታውን ለማሸነፍ መሞከር ይኖርብናል ... ትልቁ ችግራችን ምርጥ ተጨዋቾቻችን በጉዳት አለመኖራቸው ነው።"
"አሁን ላይ ሰዎች ተጨዋቾችን ለምን ከጨዋታ ጨዋታ እንደምናቀያየር የተረዱ ይመስላል ... እንደ እኔ ሀሳብ ዩሮፓ ሊግ ከሻምፒዮንስ ሊግ በበለጠ ከባድ ውድድር ነው።"
"የጨዋታዎቹን ክብደት እያወዳደርኩ ሳይሆን ሀሙስ ተጫውተክ ቅዳሜ እና እሁድ ወደ ሊግ መርሐ ግብር መመለስ ማለት እጅግ ፈታኝ ነው።"
"እሁድ ማሸነፍ አለብን የዚህ የውድድር አመትን እንደምንም ካለፍን በኋላ ለሁሉም ነገር ዝግጁ እሆናለው !!"
"የትኛውም ተጨዋች በእሁዱ ጨዋታ የመሰለፍ እድል ሊኖረው ይችላል ... ልምምዳቸውን በተገቢ ሁኔታ ካከናወኑ ሁሉም የመሰለፍ እድል የሚኖራቸው ይሆናል ።"
"ቺዶ ኦቢ በእሁዱ መርሐ ግብር የመጫወት እድል ይኖረዋል።"
"በዚህ የውድድር አመት ወደ ሜዳ መመለስ የማይችሉት ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና አማድ ዲያሎ እንደሆኑ አስባለሁ ሆኖም በአማድ ዙርያም ቢሆን በውድድር አመቱ የመጨረሻ ወር ላይ የሆነ ነገር ሊኖር ይችላል ።"
"ምንም ነገር መናገር አልፈልግም ሆኖም አማድ ዲያሎ የውድድ አመቱ ከመጠናቀቁ በፊት የመመለስ እድል ሊኖረው ይችላል ።"
"ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ግን ሙሉ በሙሉ ከውድድር አመቱ ውጪ እንደሆነ ሆኘ መናገር እችላለሁ ።"
"በሀሪ ማጓየር ላይ ጠንቃቃ ልንሆን ይገባል ማኑዌል ኡጋርቴ በእሁዱ ጨዋታ እንደሚመለስ እንጠብቃለን .... ሉክ ሾው እና ሜሰን ማውንትም በቅርቡ ወደ ሜዳ ሊመለሱ የሚችሉበት እድል አለ ።"
"እሁድ ሁሉንም እንመለከታለን ከዛ በኋላ ሁሉንም ታረጋግጥላችሁ .... ተጨዋቾች የሚመለሱ ይሆናል በተለይ ሜሰን ማውንት ከውድድር አመቱ ማብቂያ በፊት የሚመለስ ይሆናል ።"
#ይቀጥላል
@Man_United_Ethio_Fans@Man_United_Ethio_Fans