ቨርቹዋል ኦቲዝም ምንድነው?
ቨርቹዋል ኦቲዝም ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በብዛት ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት በመጠቀም የሚፈጥረ ሁኔታ ነው።
ከሶስት አመት በታች የሆኑ ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት የሚጠቀሙ ልጆች የተለያዩ የባህርይ እክሎች እና የተግባቦት እክሎች ያጋጥማቸዋል።
የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች፦
- ከፍተኛ እንቅስቃሴ (እረፍት የለሽ መሆን)
- ትኩረት ማድረግ አለመቻል
- ጨዋታዎች ላይ ፍላጎት መቀነስ
- ማህበራዊ መስተጋብር ወይም ተግባቦት አለመኖር
- ተለዋዋጭ ስሜት
- የመረዳት እክል
- የንግግር እና ቋንቋ መዘግየት
- የተገደበ የአይን ግንኙነት እና ማህበራዊ መስተጋብር
- ተደጋጋሚ ባህሪያት ወይም የተገደበ ፍላጎት
- ስሜትን የማቋቋም እክል
- ለነገሮች ስሜታዊነት (sensitive)
የቨርቹዋል ኦቲዝም መንስኤ፦
ቨርቹዋል ኦቲዝም ህፃናት በሞባይሎች፣ በታብሌት፣ በቴሌቭዥን፣ በኮምፒውተሮች እና በላፕቶፕ ስክሪን ላይ የረዘመ ጊዜ ሲያሳልፉ የሚፈጠር ሁኔታ ነው።
የቨርቹዋል ኦቲዝም ቴራፒዎች፦
- በዋነኛነት የባህርይ ቴራፒ እና የስፒች ቴራፒ
- የስክሪን ጊዜን ማቆም ወይም መገደብ
- የአካል እንቅስቃሴዎችን መጨመር
- ፊት ለፊት የሚናገሩበትን መንገድ መፍጠርና ማስተዋወቅ
- ምቹና ደጋፊ አካባቢ መፍጠር
በማህሌት አዘነ (ስፒች ላንጉጅ ቴራፒስት)
@melkam_enaseb