ላል፡፡
ቅዱስ ዳዊት "ጽዮንን ክበቧት እቀፏትም" በማለት እንደተናገረው በበዓላት ቀናት ቤተክርስቲያንን ከቦ ማደር የተለመደ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ለበዓል ወደ ቤተክርስቲያን ከመጡት ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተኝተው ሳለ "ሕልመ ሌሊተ" ታይቷቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ መልዐከ እግዚአብሔር ከእንቅልፋቸው ሳይነቁ ከቤተክርስቲያን አውጥቶ አርቆ ከውጭ አስተኝቷቸዋል፡፡ ሰዎቹም በነቁ ጊዜ "ሕልመ ሌሊት" እንደ መታቸው ከቤተ ክርስ
ቲያንም የእግዚአብሔር መልዐክ እንዳወጣቸው አስተዋሉ፡፡ ይህ ታሪክ በእመቤታችን የተአምር መጽሐፍ ተጽፎ የሚገኝ ሲሆን "ህልመ ሌሊት" ያገኘው ሰው ወደ ቤተመቅደስ መግባት እንደሌለበት ተግባራዊ ትምህርትን ያስተላልፋል፡፡ በተጨማሪም በመኝታ ወቅት ሕልመ ሌሊትን ጨምሮ ልዩ ልዩ ነገሮች ሊከሰቱ ስለሚችሉ በቤተመቅደስ መኝታ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
የፍትህ መንፈሳዊ አንድምታ መጽሐፍ ስለ ጸሎት በተናገረበት አንቀጽ ከመኝታ ተነስተው ስለሚፈጸሙ ጸሎተ ነግህ(ጠዋት 12ሰዓት) እና ጸሎተ መንፈቀ ሌሊት(ለሊት 6ሰዓት) እንዲህ ብሏል፡፡ "የነግሁንና (የንጋቱንና) የመንፈቀ ሌሊቱን ጸሎት እጃቸውን ከታጠቡ በሁዋላ ይጸልዩ በዚያ ሰዓት ውኃ ባያገኙ እፍ ብለው በአፋቸው በሚወጣው ምራቅ እጃቸውን አሽሽተው ያማትቡ" ማለት ነው፡፡
ፍትሐ ነገስት መንፈሳዊ ከመኝታ ተነስተው ስለሚፈጸሙ ሁለቱ የጸሎት ጊዜያት መተጣጠብ ያም ባይሳካ ምራቅን እንትፍ ብሎ መተሻሸት አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ሲያትት፦ "ሰው ከተኛ ዝንየት አይጠፋምና" በማለት ይገልጻል፡፡ ምናልባት ዝንየት ሊያገኘው ይችላል ተብሎ ሰው ሁሉ ከመኝታው በሁዋላ የሚያደርገውን ጸሎት ተጣጥቦ እንዲጸልይ ከታዘዘ ዝንየት እንዳገኘው እርግጠኛ የሆነ ሰው እንዴት የግድ መተጣጠብ ያስፈልገው ይሆን? አንዳንድ መምህራንና አባቶች በመኝታ ልብስ ጸሎት እንዳናደርግ የሚከላከሉትም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
"ሕልመ ሌሊት" መፍትሔ አለው??
ብዙ ሰዎች ተግቶ ለመጸለይ፣ ለማስቀደስና ለመቁረብ በወሰኑ ጊዜ ሕልመ ሌሊት እንቅፋት እየሆነ ይፈተኑበታል፡፡ በእርግጥ መብላትና መጠጣት ሳያቆሙ ሙሉ ለሙሉ ከሕልመ ሌሊት መለየት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ የሚቻል ነገር አይደለም፡፡ ለተአምራት ያህል ከሕልመ ሌሊት ፈጽሞ የተለዩ አንዳንዶች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ፦ በተአምረ ማርያም ላይ በልጅነቱ የመነኮሰ አንድ ሕፃን ነበር፡፡ ወደ ወጣትነትም በሚሸጋገርበት ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ድቀት አገኘው(ህልመ ለሊት)፤ ድቀቱም በሕልሙ ነበር፡፡ ዝንየት መታው ማለት ነው፡፡ ከመኝታውም በነቃ ጊዜ ግን ነብሱን "የፍትወትን ጣዕም ዛሬ ቀምሰሻልና ወዮልሽ" እያለ ይወቅሳት ጀመረ፡፡ ስለ መጪው ዘመኑ ወደ እመቤታችን በፍርሃት እየጸለየ ማለደ እንጂ በገጠመው ነገር ተደንቆ ደሰ ስላልተሰኘ፣ ስላልፈለገው በእመቤታችን አማላጅነት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሕልመ ሌሊትን ሳያይ ኖረ፡፡
ሀ.አባ ኢሳይያስ የተባለ መነኩሴ በመጽሐፈ መነኮሳት ስለ ሕልመ ሌሊት እንዲህ ብሏል፡፡ "ሌሊት በሕልም ከሴት ጋር የተገናኘህ መስሎህ ዘር ቢወርድብህ በቀን አታስባት"፡፡ እንዲህ ማድረግህ ደግሞ በሕልም የተመለከትከውን በእውን እያሰብከው ደስታ ከማድረግ ይጠብቅሃል፡፡ ሕልምህን ደስ እየተሰኘህበት መላልሰህ ብታስበው ግን በነቢብና በገቢር ወደ መፈጸሞ ያደርስሃል፡፡ ስለዚህ ከሕልመ ሌሊት ፈተና ለመዳን አንዱ መፍትሔ ያዩት ሕልምን በእውን ደስ እየተሰኙ መላልሶ አለማሰብ ነው፡፡
ለ.፨ ህልመ ሌሊት በምታይበት ጊዜ ከነቃህ ቸል ብለህ ተመልሰህ አትተኛ "አላ ተንሰእ ፍጡነ" "ፈጥኘህ ተነስ እንጂ" ፈጥነህ ተነሳና ተጣጥበህ ጸሎት አድርስ፡፡ ከተቻለህ ስገድ ባይቻልህ ግን የባሕሪህን ድካም ፈጣሪህ ያውቀዋልና ይቅር በለኝ፣ እርዳኝ፣ አድነኝ እያልክ ወደ እግዚአብሔር ለምን፡፡ እንዲህ በማድረግህ የሰይጣንን መንገድ ትዘጋበታለህ፡፡ ቸል ብለህ ብትተኛ ግን አንድ ጊዜ መንገድ ሰብሮ የሄደ ውሃ ካልዘጉበት በቀር በመጣ ቁጥር በዚያው እንደሚመላለስ አንተንም ሰይጣን እንዲሁ መላልሶ በሕልመ ሌሊት ያጠቃሃል፡፡
ሐ.፨ ሌላው ከሕልመ ሌሊት ለመዳን ዋነኛው መፍትሔ ውኃ በብዛት አለመጠጣት ነው፡፡ ይህን መንገድ መከተል ጥሩ መፍትሔ መሆኑን መጽሐፈ መነኮሳት ሲመሰክር "እንደ ውሃ ጥም አካልን የሚያደርቅ፣ ከሕልመ ሌሊትና ከዘር መፍሰስ የሚከለክል፣ በመዓልት ሐልዮ ኃጢአትን የሚያጠፋ የለም፡፡" ማለት ነው፡፡ (ፊልክ.ክፍ.፫ተስእ.፴፰)
መ.፨ በሕልመ ሌሊት በተደጋጋሚ እንዳትጠቃ ወደ ዝሙት ከሚያመራ ማናቸውም ነገር ሽሽ፡፡ የምታያቸውን ፊልሞች፣ ንባቦች፣ ሌሎችንም ነገሮች በጥንቃቄ መርምረህ ለፍትወት የሚያጋልጡትን ሽሻቸው፡፡ ዝሙት ቀስቃሽ ነገሮችን አለማየት፣ አለመስማት፣ አለማንበብ። ከዚያ ይልቅ ደጋግ መንፈሳዊ መጻሕፍቶችን ለማንበብ ትጋ፡፡ ጠንክሮ መጸለይን አትተው እንዲህ በማድረግህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ረድኤትን ታገኛለህ፡፡
ሠ.፨ ከመኝታህ በፊት ጠግቦ ላለመብላት ሞክር፡፡ ትኩስና የሞቁ ነገሮችን ላለመውሰድ ተጣጣር፡፡ እንዲህ ያደረክ እንደሆነ ቅዱስ ዳዊት "በሰላም እተኛለው አንቀላፋለው"ለ እንዳለ አንተም የሰላም እንቅልፍ ትተኛለህ፡፡
ረ.፨ ከመንፈሳዊ መምህራን አበው ካህናት ጋር እየተማከሩ በሚያቀርቡት የመፍትሔ ሐሳብ መጓዝ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ ሊጠነቀቁበት የሚገባ አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም የምናማክረው ሰው ምሥጢራችንን ለመያዝ የታመነና በምንነግረውም ነገር ራሱ ወደ ፈተና ሊገባ የማይችል በሕይወቱ ብዙ ተሞክሮ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡