ከ890 በላይ እስረኞች በምግብ እና ውሀ ብክለት ታመሙ፣ ሟቾችም እንዳሉ ተሰምቷል
(መሠረት ሚድያ)- በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ አቅራቢያ 'ጮሬሳ' ተብሎ በሚጠራው ካምፕ ውስጥ ከ890 በላይ የፖለቲካ እስረኞች በምግብ እና በውሃ ብክለት ምክንያት መታመማቸው ታውቋል።
መሠረት ሚድያ ከእስረኞች ቤተሰቦች የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ እስረኞች መሞታቸውም ተረጋግጧል።
በሽታው የተቀሰቀሰው በዚህ ሳምንት የካቲት 6/2017 ዓ/ም መሆኑን የተናገሩት የታሳሪ ቤተሰቦች ለእስረኞቹ የሚቀርበው ውሃ ከወንዝ እየተቀዳ በመሆኑ ለበሽታው ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ብለዋል።
ወደ እስረኞች ካምፕ ከፌደራል ፖሊስ እና ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ውጭ መግባት የተከለከለ በመሆኑ የሕክምና አገልግሎት ማገኘት እንዳልቻሉም ቤተሰቦቻቸው ጨምረው ተናግረዋል።
እስረኞቹ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን የፋኖን ኃይል ትደግፋላችሁ በሚል ከመስከረም ወር ጀምሮ ከተለያዩ የአማራ ክልል ወረዳዎች በማሰባሰብ ከኮምቦልቻ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኛው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
ከእስረኞቹ ውስጥ 220ዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ዋስትና የተፈቀደላቸው ቢሆንም ታሳሪዎቹን የተረከበው የፌደራል ፖሊስ እስረኞቹን መልቀቅ የሚችለው መከላከያ እንጂ ፍርድ ቤት አይደለም በሚል ሊለቃቸው ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ተብሏል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia