የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ ያጣውን የገንዘብ ድጋፍ ለማካካስ ህዝብን ማስከፈል ሊጀምር መሆኑ ተሰማ
- ኢትዮጵያ በድጋፉ መቆም በከፍተኛ ደረጃ ከተጎዱ የአለም ሀገራት 3ኛ ደረጃን ይዛለች
(መሠረት ሚድያ)- የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በዩኤስኤድ (USAID) እና ሌሎች ተቋሞች በኩል ኢትዮጵያን ጨምሮ ለበርካታ የአለም ሀገራት ይሰጥ የነበረው ድጋፍ መቆሙን ተከትሎ ከፍተኛ መደናገጥ እና አሳሳቢ ክስተቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የአሜሪካንን ድጋፍ ሲያገኙ ከነበሩ ሀገራት አንዷ ስትሆን በተለይ የጤናው ዘርፍ እና የሰብአዊ እርዳታ ከ80 ፐርሰንት በላይ በአሜሪካ ድጋፍ ላይ የተንጠለጠለ ነበር፣ በድጋፉ መቆም በከፍተኛ ደረጃ ከተጎዱ የአለም ሀገራት 3ኛ ደረጃን ይዛለች።
ባለፉት ሶስት አመታት 2.89 ቢልዮን ዶላር (በአሁን ስሌት 353 ቢልዮን ብር ገደማ) የውጭ እርዳታ ያገኘው የኢትዮጵያ መንግስት በትራምፕ አስተዳደር ድጋፍ መቆም የተፈጠረውን ከፍተኛ ጫና ወደ ህዝብ ለማስተላልፍ መወሰኑን መሠረት ሚድያ ሰምቷል።
"የዛሬ ሶስት አመት 1.5 ቢልዮን ዶላር የነበረው የውጭ ድጋፍ ዘንድሮ ወደ 190 ሚልዮን ዶላር አሽቆልቁሏል። ይሄ ማለት እንደ ወባ፣ ቲቢ፣ ኤችአይቪ ላሉ ታካሚዎች የሚውሉ መድሀኒቶችን ወደ ሀገር ገዝቶ የማስገባት አቅም መንግስት የለውም። ሌላው ቀርቶ ለወላድ እናቶች የሚውሉ መድሀኒቶች እና ቁሳቁሶች በእርዳታ የሚቀርቡ ነበሩ" ያሉን አንድ ከፍተኛ የፌደራል መንግስት የስራ ሀላፊ ችግሩ በመጪው ቀናት መታየት እንደሚጀምር ጠቁመዋል።
"ይህን ችግር ለመጋፈጥ ሲባል ለአደጋ ስጋት መዋጮ የሚውል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል" ያሉት ሀላፊው የመንግስትም ይሁን የግል ሰራተኛ ከደሞዙ ብር እንዲያዋጣ እንደሚገደድ አረጋግጠዋል።
ለፓርላማ የቀረበው ረቂቅ ህጉ የመንግስትም ይሁን የግል ተቋማት "የአደጋ ስጋት ፈንድ" የሚል ክፍያ ከህዝብ እንዲሰበስቡ እና ለመንግስት እንዲያስገቡ ያዛል። ከዚህም በተጨማሪ ደሞዝተኛ ተቀጣሪዎች ከክፍያቸው ላይ በየወሩ ብር እንዲያዋጡ ህጉ ያስገድዳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን "የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅቶች (USAID) እንዴት ነው አፍሪካን ከተኛችበት እየቀሰቀሳት ያለው?" በሚል ትናንት ባቀረበው ዘገባው የእርዳታ ድርጅቱን “የበግ ልብስ የለበሰ ተኩላ” በማለት አንዲት የቀድሞ የአፍሪካ ዲፕሎማት ንግግርን አቅርቧል።
"እነዚህ ድርጅቶች የጤና እና የትምህርት ዘርፍን ለማሻሻል እንደመጡ ይገልጻሉ፤ ነገር ግን በዚህ ረገድ የመጣ ለውጥ የት አለ?" በማለት የሚጠይቁት ግለሰቧ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ያሉ ጤና ጣብያዎች እና የስደተኛ ካምፖች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በውጭ ድጋፍ እንደሚደጎሙ ሳይጠቅሱ አልፈዋል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia