በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከሚታገሉ ሰዎች የምሰማው አንድ አባባል አለ።
“ከሰይጣንም ጋር ቢሆን ተባብረን አገዛዙን እንጥለዋለን።”
ወይም “ሰይጣንም ቢሆን እንተባበር ካለን ምን ጨነቀን። ይሄ ፖለቲካ ነው። ፖለቲካ ደግሞ እንደዚህ ነው” ይላሉ።
ግን ግን ሰይጣን ከመቼ ጀምሮ ነው ከበጎ ዓላማ ጋር የሚተባበረው? ቢተባበር እንኳ የእርሱ ክፉ ዓላማ መጨረሻ ላይ እንደሚሳካ እርግጠኛ ሳይሆን ይተባበራል?
ይገባኛ ሰይጣን ስትሉ እንደ ሰይጣን ያለ ክፉ ለማለት እንደሆነ።
ግን የትኛውም ትብብር አንዱ የስኬቱ ምንጭ እኮ ትብብሩ ውስጥ ያሉ የስብስቦቹ ጥሩ መሆን ነው።
መልካሙን ስብስብ አንዱ ክፉ አካል እንኳ ይበጠብጠዋል። አይደለም ሄደን ክፉ ስብስብ ውስጥ ገብተን። በሀገራችንም ሰዎች ስለኛ በደንብ ለማወቅ ከማን ጋር እንደዋልን ነው የሚጠይቁን። አዋዋላችን ማንነታችንን ይወስናል።
ከሰይጣን ጋር ውል ተፈራርሞ፣ ያልተከዳ አይቼ እስካሁን አላውቅም። አሰፋ ጨቦ “ኢትዮጵያኖች የማይመጣ ነገር መጠበቅ ይወዳሉ” ይላል። ፖለቲካ ለመስማት ከበቃውበት ዕድሜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ከሰይጣንም ጋር ቢሆን አገዛዙን ለመጣል እንሰራለን ሲሉ ነው የምሰማው። እስካሁን ሰይጣን ነው በመጨረሻ እየረታ ያለሁ። የማይመጣ ነገር መጠበቅ ማለት ይሄ ነው።
ግድ የለም ከሰይጣን ውጪ ሞክሩት።