ልሳሳት እችላለሁ። ብዙ ሰው ሲጸልይ “የተራቡትን አስባቸው።”ይላል። በተለይ የምግብ ሰዓት ላይ።
እኔግን ይሄ ተገቢ ጸሎት አይመስለኝም።
ትክክለኛው የጸሎት ቅርጽ መሆን ያለበት “የተራቡትን ሰዎች እንድናስባቸው እርዳን” ነው መሆን ያለበት።
እግዚአብሔር የተራቡትን ለመመገብ የኛ አሳሳቢነት አያስፈልገውም። እኛ ግን የተራቡትን፣ የተቸገሩትን ለመርዳት እግዚአብሔር ከስግብግብነት ሊያላቀን እና የመራራትን አቅም ሊሰጠን ይገባል።
ስለዚህ ስንበላ ለሌሎች ማካፈል እንድንችል ነው ስለ እኛ ልብ መለመን ያለብን።
ጌታ ከትንሣኤ በኋላ የራበው፣ ምግብም የፈለገ ሰው መስሎነበር ወደ ሐዋርያት የመጣው። ዮሐንስ ወንጌል 21። ለራሳቸው ምግብ የሌላቸው ሐዋርያት ግን እንዴት በሚገርም ትህትና አናገሩት። ጌታ መሆኑን ሳያውቁ። ያ የመራራት ልብ ራሱን እንዲገልጥላቸው አስቻለ።
ይሄ ግን ቤተክርስቲያን ከምታደርገው ምልጃ ይለያል። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ልብ ወደ ኃጢአተኞች ዘንበል እንዲል፣ በኃጢአትም ምክንያት የተራቡትን እንዲያስብ በሰጣት ስልጣን ምልጃ ታቀርባለች።