ሁለት ወታደሮች መንገድ ላይ ሲደባደቡ ብታዩ እና ያንን ድብድብ ለሰዎች (በዚያ ላልነበሩ) መንገር ብትፈልጉ፣ ምንድነው ብሏችሁ የምታወሩት?
ሁለት ሰዎች ተደባደቡ ብላችሁ? ወይስ ሁለት ስማቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ተደባደቡ?
በፍጹም።
ይልቁንስ፥ ሁለት ወታደሮች ተደባደቡ ነው የምትሉት።
የፌዴራል ፖሊስ ከሆኑም ሁለት የፌዴራል ፖሊሶች ተደባደቡ ነው የምትሉት። በዚህም ወታደሮቹን ብቻ ሳይሆን፣ ተቋሙንም ትገመግማላችሁ። ትታዘባላችሁ።
ክርስቲያን ሆነን ሰዎች ላይ ክፋትን ስንሰራ፣ ሰዎች እነዛ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለ ነገር ፈጸሙ ብለው ነው የሚያወሩት። ከዛ ሃይማኖት ሁሉ ውሸት ነው ለሚሉ ሰነፎች ዕድል እንሰጣለን። በተለይ በክርስትና ስም ለሚነግዱ ሰዎች፥ የሰዎችን ብቸኛ ተስፋ ነው የምናቆሽሸው።
በስደተም ያለን ኢትዮጵያኖች፣ በስደት ባለንበት ሀገር ላይ የምንሰራው ወንጀል እና ክፋት፥ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ነው የሚያስነቅፈው። እነዛ ኢትዮጵያውያን ነው የሚያስብለው።