አውሮፓ ለባለፉት አስርት ዓመታት እምነት አልባነትን ሞከረ። በአውሮፓ እንደኖረ ሰው፣ በየሜትሩ ድንቅ ሕንጻ ቤተክርስቲያናትን ከምዕመን ውጪ እንዳየ ሰው፤ አውሮፓ ወደ እግዚአብሔር ይመለሳል ብዬ ገምቼ አላውቅም ነበር። ያለቀ የደቀቀ ነበር የመሰለኝ። በርግጥ እኔም በአውሮፓ ስኖር ኢአማኒነት ጎትቶኝ ነበር።
አውግስጢኖስ እንዳለው "ነፍሴ አንተን እስክታገኝ ድረስ እንዳትረካ አድርገህ ፈጠርካት።"
የሰው ልጅ ነፍስ ካለክርስቶስ እንዳትረካ ተደርጋ ተፈጥራለች። ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እስክታገኝ በፍልስፍና፣ በዝሙት፣ በመዳራት በዚህ ዓለም ስኬት እና ዝና መንገዶች ትቀበዘበዛለች።
በመጨረሻም በእነዚህ ሁሉ ረፍት እንደሌለ ስታይ ፥ እንደ አውግስጢኖስ ወደ ፈጣሪዋ ትጨዋለች። "ነፍሴ አንተን እስክታገኝ ድረስ እንዳትረካ አድርገህ ፈጠርካት" እያለች።
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አራት እንዳለችው ሳምራዊቷ ሴት ፥ እንስራችንን ከዚህ ዓለም ውሃ ዳር ትተን የነፍሴን ውሃ ክርስቶስን አገኘውት እያልን እንቦርቃለን። አውሮፓ እንደ ሳምራዊቷ ሴት ነው የሆነችው። ትራምፕ እግዚአብሔር ይስጠው። የእርሱ ክፋት፣ ንቀቱ እና ትዕቢቱ ፥ የአውሮፓን ልብ ወደ ክርስቶስ መለሰው።
ክፋት እንዴት እንደሚሸነፍ አታውቁም። ግን ክፋት በራሱ ምክር ነው የሚወድቀው።
በሰይፍ አይደለም። በሰልፍ ብዛትም አይደለም።
(ፎቶ ዓርብ ሴፕቴምበር 25፣ 2026 ፖፕ ሊዮን ሊቀበል የወጣው የፓሪስ አንድ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ነው።)