TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
Mulualem’s View

30 Sep, 03:12

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

ብዙ ጊዜ የምንስተው ነገር አለ። ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት። የእኛን ድርሻ እንስተዋለን። የኛን ቦታ ትተን የፈጣሪን ቦታ ለመውሰድ እንቋምጣለን።


በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሁለት ላይ በዚህ ዓለም ላይ ሊገኙ የሚችሉ መልካም ሰዎች ሁሉ የተገኙበት ሠርግ አለ። በዛ ሠርግ ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናቱ እና ደቀመዛሙርቱ ተገኝተው ነበር።


የቃናው ሠርግ።


ከሴቶች ሁሉ የተባረከችው ከሰው ሁሉ በላይ ወደ ተባረከው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጣች። "ሠርገኞቹ ወይን አልቆባቸዋል"ብሏ።


ምን እንደመለሰላት መስማማት አልቻልም። ምን እንዳደረገላት እንጂ። የጠየቀችውን በራሱ መንገድ አደረገላት። እርሷ ግን ሄዳ ደቀመዛሙርቱን "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።"


እርሱም "ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው።" ደቀመዛሙርቱም ሞሉት። እንደተባሉት።


ከዛ ለሠርግ አዘጋጁ "ቅዱ እና ስጡት" አለ። አዘጋጁ ሲሰጡት ውሃው ወይን ሆኖ ነበር። ተራም ወይን አልነበረም። ከበፊተኛው የበለጠ እንጂ።


በዚህ ዓለም የሰው ልጅ ድርሻ ድንግል ማርያም እንዳለችው "የሚለንን መስማት ብቻ ነው።"


መቀየር የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ድርሻ ነው። በዚህ በቃና ሠርግ ቤት የነበሩት ማናቸውም ውሃውን ወደ ወይን እንቀይር አላሉም።


ወደ ጌታ የቀረበች ስለ ጎደለው ነገር አሳሰበች። አገልጋዮች ቃሉን ሰምተው አደረጉ። መቀየር ግን የእርሱ ድርሻ ነበር። እንዴትም እንደቀየረ እኛ አናውቅም። ያ የእርሱ ድርሻ ነው።


እኔ ፍቺ ስሰራ በጣም ብዙ የማየው ነገር ፥ ባሎች ሚስቶቻቸውን ለመቀየር ሚስቶች ደግሞ ባሎቻቸውን ለመቀየር ሲታገሉ ነው ፍቺ ላይ የሚደርሱት። የእነርሱ ድርሻ ያልሆነውን ሲሰሩ።


ብዙ ጓደኞሞች የሚጣሉትም አንዱ አንዱን ለመቀየር ሲታገል ነው።


በወላጆቻቸውም የሚናደዱ ልጆች ብዙ ጊዜ ስጠይቃቸው የሚነግሩኝ ያንን ነው። ወላጆቻቸው አቺቭመንታቸውን (achievement) እንጂ እነርሱን የማይወዱ ይመስላቸዋል። ሊቀይሯቸው ነው የሚታገሉት። የእነርሱን የሙያ ፊልድ እንዲመርጡ ፍላጎታቸውን ሊቀይሩ ሲታገሉ፣ ወላጆቹ ወደ ሚፈልጉት ባህሪ ልጆቻቸውን ለመቀየር ሲታገሉ ነው ብዙ ወላጆች የሚውሉት። ከዛ ልጆች በዚህ ምክንያት ከወላጆች ይርቃሉ። ይሸሻሉ።


የኛ ድርሻ አንድን ሰው በራሳችን መልክ መስራት አይደለም። ሰው ሁሉ በአምላኩ መልክ የተሰራ ነው። ያንንም መልክ ያንጸባርቃል። ወደ ፈጣሪው ከተጠጋ። እንጂ የኛን መልክ (ፍላጎት) እንዲያንጸባርቅ ለማድረግ መታገል ነውር ነው። የኛ ድርሻ ሰውን ማድመጥ ነው። መውደድ ነው።


ከወደድነው እንደ ድንግል ማርያም፣ ወደ ፈጣሪው ሄደን የጎደለውን ነገር እናሳስብለታለን። ከዛ አድርጉ የተባልነውን ነገር እንደርጋለን።


አድርጉ የተባልነው ደግሞ "ባልጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ነው።" እንደ ራስህ!!!


ለራሳችን ያሳየነውን ትግስት እና ፍቅር ለምናየው ሰው ሁሉ ማሳየት።

583 0 11 2 42
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot