የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እስከምሽቱ 4:00 እንዲሰጥ ተወስኗል
በአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የምትሰጡ አካላት እስከ ምሽቱ 4:00 የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ 4ተኛ ዓመት፣ 4ተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ መሠረት ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የምትሰጡ አውቶቡሶች፣ ሚዲ ባስ እና ሚኒ ባሶች ቢሮው ባወጣው መደበኛ ቀን በሚትሰሩበት መስመር እና ቀን ላይ በሚከፈለው ህጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከምሽቱ 4:00 አገልግሎት እንድትሰጡ ቢሮው ያስታውቃል።
ስለሆነም የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ይህን በሚገባ በመረዳት እስከምሽት 4:00 አገልግሎት እንድታገኙ እና የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እንዲሁም የሚመለከታችሁ አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ቢሮው ጥሪ ያስተላልፋል።
Via @mussesolomon