በህንድ የኮምፒውተር ባለሙያው ለአለቃው ስራ ማቆም እንደሚፈልግ ከመናገር ይልቅ አራት ጣቶቹን ቆረጠ
የ32 ዓመቱ ህንዳዊው ሰው በዘመድ ኩባንያ ውስጥ የኮምፒተር ኦፕሬተር ሆኖ ሲሰራ የነበረ ሲሆን የግራ እጁን አራት ጣቶችን እንደቆረጠ አምኗል።
አይሆንም ማለትን መማር ቀላል ይመስላል፣ ነገር ግን ለአንዳንድ ሰዎች፣ አይሆንም ወይም እምቢ ከማለት ይልቅ የገዛ ህይወታቸውን የበለጠ ከባድ አደጋ ላይ እስከ መጣል ሊሄዱ ይችላል። ለአለቃው ስራውን መልቀቅ እንደሚፈልግ ላለመናገር በግራ እጁ ላይ አራት ጣቶቸን እንዲቆረጥ ያደረገው የጉጃራቱ ሰው አደጋ እንደደረሰበት ሲያስመስል ቆይቷል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ማዩር ታራፓራ የግራ እጁ አራት ጣቶች መቆረጣቸውን ለማሳወቅ በትውልድ ከተማው ሱራት ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ አምርቷል። ሞተር ብስክሌቱን እየጋለበ ወደ ጓደኛው ቤት እየሄደ እንደነበር ተናግሯል።
ታዲያ በድንገት ራስን የማዞር ስሜት ተሰማው እና በመንገዱ ዳር ላይ መውደቁን ገልጿል። ከ10 ደቂቃ በኋላ ከእንቅልፉ ሲነቃ የግራ እጁ አራት ጣቶች ተቆርጠዋል። ፖሊሶች መጀመሪያ ላይ የሰውዬው ጣቶች ለጥቁር የአስማት የአምልኮ ሥርዓቶች እንደተቆረጠ በማመን እርሱ ከተናገረው ውጪ ተጠራጥረው ነበር። ነገር ግን ምርመራቸው ማዩር ላይ ጫን አድርገው ሲቀጥሉ ያልጠበቁት ሆኖ ተገኝቷል።አስገራሚው ጉዳይ ወደ ከተማው የወንጀል ቅርንጫፍ ከመዛወሩ በፊት በሱራት ፖሊስ ጣቢያ ተመዝግቧል። መርማሪዎች ተጎጂው እንደወደቀ በተናገረበት አካባቢ የክትትል ካሜራ ቀረጻ እና የዓይን እማኞችን ማጣራት ሲጀመር ግን እርሱ የተናገረውን መረጃ ማግኘት አልቻሉም።
Via @mussesolomon