ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ ጋር በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት መስማማታቸው ተገለጸ
ሀገራቱ በማዕከላዊ ባንኮቻቸው በኩል ገንዘቦችን በመለዋዋጥ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት ነው የተስማሙት።
ከክሪምሊን የወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው ይህን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር በሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመገበያየት ስምምነት ላይ የደረሱ ሀገራት ቁጥር 40 ደርሷል፡፡
እንደ አልጄሪያ፣ ግብፅ፣ ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በመስከረም 2023 በሩሲያ መንግስት የጸደቀው የመጀመሪያው ዝርዝር ውስጥ ነበሩ።
የአርጀንቲና፣ የካምቦዲያ፣ የላኦስ፣ የሜክሲኮ፣ የናይጄሪያ፣ የቱኒዚያ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተወካዮች በመገበያያ ገንዘብ ንግድ እንዲሰማሩ አዲስ ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
የሩሲያ መንግስት መመሪያው የሩስያ ኢኮኖሚን በመገበያያ ገንዘብ የሚከፍለውን ፍላጎት ለማሟላት እና ወዳጃዊ እና ገለልተኛ መንግስታት ብሔራዊ ገንዘቦችን በቀጥታ በመለዋወጥ የስርዓቱን ውጤታማነት እንደሚያሳድግ አስታውቋል፡፡
Via @mussesolomon