#ደጅሽ_ላይ_ቆሜ
ደጅሽ ላይ ቆሜ ስለምንሽ
ባርኪኝ እናቴ ማርያም ስልሽ
ተደላደለልኝ ህይወቴ
ባንቺ በእናቴ በእመቤቴ
አንቺ በመሆንሽ የህይወቴ ፋና አልፈራም ጨለማ ብርሃን አለኝና
አይጠፋም ዘላለም ስምሽ ከአንደበቴ
አለ በደሜ ውስጥ ፍቅርሽ በህይወቴ
አልቀርም ደጅሽ ለዘለዓለም/2/
ካንቺ ሚለየኝ ማንም የለም/2/
አዝ ======
እጅግ የተከፋ ደካማ ሰው አለ
መቅደስሽ የቆመ አማልጂኝ እያለ
ይቁም ይሄ ልጅሽ ሃዘን የሰበረው
ካንቺ በቀር ወገን መጠጊያ የሌለው
ያንሳው ኪዳንሽ ከውድቀቱ/2/
ያርግ በእጆችሽ ያ ጸሎቱ/2/
አዝ =====
ጽልመት የለበሰ ፈታኝ አደከመኝ
የምቋቋምበት ጉልበት አስፈለገኝ በርትቼ እንድፀና ሳትጎዳ ነፍሴ
ሁኚኝ እናቴ ሆይ ግርማዬ ሞገሴ
ልፅና ደግፊኝ እመቤቴ/2/
ይውለቅ ከእጄ ላይ ሰንሰለቴ/2/
አዝ ======
አበው የለበሱሽ የክብራቸው ካባ
መዓዛሽ የሚስብ የሮማን አበባ
ለውጪው እናቴ የህይወቴን ቃና
ባዶ ጋኔን ምልጃሽ ወይን ያስሞላውና
አፅጂልኝ በእጅሽ ማድጋዬን/2/
በወይን አስሞዪው እንስራዬን/2/
ሊ/መ/ቀ ምንዳዬ ብርሃኑ
ደጅሽ ላይ ቆሜ ስለምንሽ
ባርኪኝ እናቴ ማርያም ስልሽ
ተደላደለልኝ ህይወቴ
ባንቺ በእናቴ በእመቤቴ
አንቺ በመሆንሽ የህይወቴ ፋና አልፈራም ጨለማ ብርሃን አለኝና
አይጠፋም ዘላለም ስምሽ ከአንደበቴ
አለ በደሜ ውስጥ ፍቅርሽ በህይወቴ
አልቀርም ደጅሽ ለዘለዓለም/2/
ካንቺ ሚለየኝ ማንም የለም/2/
አዝ ======
እጅግ የተከፋ ደካማ ሰው አለ
መቅደስሽ የቆመ አማልጂኝ እያለ
ይቁም ይሄ ልጅሽ ሃዘን የሰበረው
ካንቺ በቀር ወገን መጠጊያ የሌለው
ያንሳው ኪዳንሽ ከውድቀቱ/2/
ያርግ በእጆችሽ ያ ጸሎቱ/2/
አዝ =====
ጽልመት የለበሰ ፈታኝ አደከመኝ
የምቋቋምበት ጉልበት አስፈለገኝ በርትቼ እንድፀና ሳትጎዳ ነፍሴ
ሁኚኝ እናቴ ሆይ ግርማዬ ሞገሴ
ልፅና ደግፊኝ እመቤቴ/2/
ይውለቅ ከእጄ ላይ ሰንሰለቴ/2/
አዝ ======
አበው የለበሱሽ የክብራቸው ካባ
መዓዛሽ የሚስብ የሮማን አበባ
ለውጪው እናቴ የህይወቴን ቃና
ባዶ ጋኔን ምልጃሽ ወይን ያስሞላውና
አፅጂልኝ በእጅሽ ማድጋዬን/2/
በወይን አስሞዪው እንስራዬን/2/
ሊ/መ/ቀ ምንዳዬ ብርሃኑ
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊