የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድና የማኔጅመንት የምክክር መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተደረገው ምክክር የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የቦርዱ ሊቀ መንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በሩብ ዓመቱ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ መስተካከል በሚኖርባቸው ላይ በጋራ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በምክክር መርሐ ግብሩ ላይ የባንኩ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በላይ ጎርፉ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ በሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ ታዳሚዎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በመጋበዝ የምክክር መድረኩን አስጀምረዋል፡፡
በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲጫወትና ግዴታውን እንዲወጣ እንዲሁም ባንኩን ወደ ተሻለ ከፍታ ማድረስ እንደሚገባ በመስማማት የዕለቱ የምክክር መድረክ ተጠናቅቋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ፤ የማኔጅመንት አባላት እና የመምሪያና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡