አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሔኖክ ከበደ በይፋ ስራ ጀመሩ።
በቅርቡ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሹመታቸውን የተቀበሉት አቶ ሔኖክ ከበደ ወደ ቢሯቸው ሲገቡ በባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድና በማኔጅመንት አባላት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ''የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ እምነት ጥሎብኝ ለዚህ ሃላፊነት ስላጨኝ፤ ደግሞም ስለመረጠኝ ከልብ አመሰግናለሁ'' ብለዋል።
''የንብ ባንክን ማሕበረሰብ በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ'' ያሉት አቶ ሔኖክ ''በተጣለብኝ እምነት መሰረት ባንኩን ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን ወደሚገባው ላቅ ያለ ቦታ ለማድረስ ዝግጁ ነኝ'' ብለዋል።
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ በበኩላቸው አዲሱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመላው የባንኩ ማሕበረሰብ ስም ''እንኳን ደህና መጡ'' በማለት መልካም የሥራ ጊዜ የተመኙ ሲሆን ''አቶ ሔኖክ በእውቀትም ሆነ በተግባር የተፈተነና ለባንካችንም ትክክለኛና ተገቢ ሰው ነው'' ብለዋል።
''ታታሪው የንብ ሰራዊትን እየመሩም ባንኩን ለተሻለ ደረጃ እንደሚያበቁ እምነቴ ፅኑ ነው'' ብለዋል።
በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ያገለገሉት አቶ ሔኖክ ከበደ በኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን ለሰባት ዓመት ደግሞ የዲስትሪክት ማኔጀር ሆነው ሰርተዋል፡፡
በተጨማሪም በዳሽን ባንክ ከስድስት ዓመት በላይ የባንኩ ቺፍ ባንኪንግ ኦፊሰር እንዲሁም በአማራ ባንክ ለ2 (ሁለት) ዓመት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት አገልግለዋል፡፡
መልካም የሥራ ጊዜ!
መረጃውን ለሌሎች ስለሚያጋሩ እናመሰግናለን!
****
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!