ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በመሐል መርካቶ የሚገኘውን የቃቄ ውርደውት ቅርንጫፍ በአዲስ መልክ አደራጅቶ ሥራ አሰጀመረ፡፡
"የቃቄ ውርደውት" ቅርንጫፍ ስያሜ ከዛሬ 170 ዓመታት በፊት ለጾታ እኩልነት ስትታገል ከነበረች ጠንካራ ኢትዮጵያዊት እንስት ሥም የተወሰደ ነው፡፡ ባንካችንም በታሪክ ሰሪዋ ጠንካራ ሴት ስም በመሐል መርካቶ የቃቄ ውርደውት ቅርንጫፍን በመክፈት ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡
የባንኩ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ ወ/ሮ ሐረገወይን አምሳለ በሥነ ስረዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የቃቄ ውርድወት ቅርንጫፍ ተከፍቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ነባር ቅርንጫፍ ቢሆንም አደራጃጀቱ ከስያሜው ጋር የተጣጣመ ስላልነበር በአዲስ አደረጃጀት ሙሉ በሙሉ በሴት እህቶቻችን የሚመራ በመሆኑ የውርድወትን የጾታ እኩልነት ትግል ተምሳሌት እንዲሆን ታስቦ የተራጀ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አክለውም ባንካችን በዛሬው ዕለት የቃቄ ውርደውትን ቅርንጫፍ በአዲስ መልኩ በማደራጀትና መርቆ በመክፈት የተሟላና የተሻለ የባንክ አገልግሎት ለውድ ደንበኞቹ ለማቅረብ ቃል መግባቱን በመጥቀስ ቅርንጫፉ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ በይፋ ሥራ መጀመሩን አብስረዋል፡፡