እርግጡን ልንገርሽ "አፈቅርሻለሁኝ" ❤️
ህልሜን እንዳዋይሽ ህልምሽን ንገሪኝ
ህልም እንደ ፈቺው ነው እባክሽ አትፍሪኝ
ብዬ ባልኩሽ ጊዜ ህልምሽን ብትነግሪኝ
እንደዚህ ፈታሁት እ'ህ" ብለሽ ስሚኝ ።
፡
ህልምሽን ስፈታው ትርጉሙ ይኸው ነው
መጣላት ለሚለው በፍቅር መውደቅ ነው
ዕንባ ማለት ደግሞ ደስታና ፌሽታ ነው
ፈልገሽ ማጣትሽ እኔን ማግኘትሽ ነው ።
፡
ህልምሽን ነግረሽኝ እኔም ፈታሁልሽ
ህልሜን ደግሞ ስሚኝ እታለም ልንገርሽ ?!
፡
በነጭ ፈረስ ላይ አንቺ ተቀምጠሽ
እኔ ስከተልሽ እርቀሽኝ ሳለሽ
ብጣራ አትሰሚኝ ሰግረሽ ትሄጃለሽ
ምንድነው ትርጉሙ ንገሪኝ አስልተሽ ።
፡
እሷ..
ህልምህን ስፈታው እንዲህ ነው የሆነው
ካንተ እቅፍ ውጪ ሌላው ወዳቂ ነው
በፈረስ መስገሩም እድሜና ጽድቅ ነው
እውነቱን ልንገርህ ሁሉም የፍቅር ነው ።
፡
እኔ...
ህልምሽን ነገርሽኝ ህልሜንም ነገርኩሽ
ህልም እንደ ፈቺው ነው እውን ይሁን አልኩሽ
ግን .......
ግን ግን - እታለሜ .....?
ህልም ተተርጉሞ ህይወት እንዲዘራ
ነይና ልቀፍሽ አዝመራው ይዘራ
እሸት ሳለሽ ልብላሽ
እሸት ሳለው ብይኝ
እርግጡን ልንገርሽ - አፈቅርሻለሁኝ ።
----------------
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
ህልሜን እንዳዋይሽ ህልምሽን ንገሪኝ
ህልም እንደ ፈቺው ነው እባክሽ አትፍሪኝ
ብዬ ባልኩሽ ጊዜ ህልምሽን ብትነግሪኝ
እንደዚህ ፈታሁት እ'ህ" ብለሽ ስሚኝ ።
፡
ህልምሽን ስፈታው ትርጉሙ ይኸው ነው
መጣላት ለሚለው በፍቅር መውደቅ ነው
ዕንባ ማለት ደግሞ ደስታና ፌሽታ ነው
ፈልገሽ ማጣትሽ እኔን ማግኘትሽ ነው ።
፡
ህልምሽን ነግረሽኝ እኔም ፈታሁልሽ
ህልሜን ደግሞ ስሚኝ እታለም ልንገርሽ ?!
፡
በነጭ ፈረስ ላይ አንቺ ተቀምጠሽ
እኔ ስከተልሽ እርቀሽኝ ሳለሽ
ብጣራ አትሰሚኝ ሰግረሽ ትሄጃለሽ
ምንድነው ትርጉሙ ንገሪኝ አስልተሽ ።
፡
እሷ..
ህልምህን ስፈታው እንዲህ ነው የሆነው
ካንተ እቅፍ ውጪ ሌላው ወዳቂ ነው
በፈረስ መስገሩም እድሜና ጽድቅ ነው
እውነቱን ልንገርህ ሁሉም የፍቅር ነው ።
፡
እኔ...
ህልምሽን ነገርሽኝ ህልሜንም ነገርኩሽ
ህልም እንደ ፈቺው ነው እውን ይሁን አልኩሽ
ግን .......
ግን ግን - እታለሜ .....?
ህልም ተተርጉሞ ህይወት እንዲዘራ
ነይና ልቀፍሽ አዝመራው ይዘራ
እሸት ሳለሽ ልብላሽ
እሸት ሳለው ብይኝ
እርግጡን ልንገርሽ - አፈቅርሻለሁኝ ።
----------------
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery