ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ እኔም ዛሬም ከደገመኝ እርምን አላቅ ብዬ እንደገና አዬ ሰው ማመን ካመመኝ አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ተታለለ የካብኩት ተናደ ባለማወቅ ስገነባው ፈርሶ ባጸዳው ቆሸሸ እንደገና የጸዳው ደፍርሶ ወርቅ አይደለ ነገር አይጣራ በእሳት አልፈትሸው የቸገረ ነገር ግራ ገባኝ በምን ይለያል ሰው ቀድሞ አለመጠንቀቅ ጥንቱን አለመፍራት ሀይለኛ ዱላ ነው ያረፈብኝ ማገገሜን እንጃ ምን ተሻለኝ እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን ያለመረሳትሽ ሚስጥሩ ምን ይሆን
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏