ትዝታሽ ዘወትር ወደኔ እየመጣ እፎይ የምልበት ህይወቴ ጊዜ አጣ የትዝታ ስሜት ልብ ላይ ነዳጅ አይጠፋም ምን ጊዜም ይዳፈናል እንጂ ታዝኚልኝ ነበር ብታዪኝ በእውነቱ ከሰውነት ወጣሁ ትዝ ብሎኝ የጥንቱ ትዝታሽ በርቀት የሚወረወረው በድንገት ገባና ልቤን ቦረቦረው እህህ በማለት እድሜን ልጨርሰው ባይኔ እያየሁሽ ነው ሆዴን የሚብሰው እህህ ማለትን ማንም አያውቀውም ከልቡ ውስጥ ገብቶ ካላስጨነቀው እህህ ወየው ጉድ ስንት አለ በሆዴ አምቄው ነው እንጂ ኑሮዬን በዘዴ ወፊቱን አርዳችሁ ክንፏን አኑሩልኝ ስበር እኖራለሁ መቼም አልሆነልኝ ሁልጊዜ ከላይ ታች እኔ የምባዝነው የጎደለው ሞልቶ ይሆናል ብዬ ነው ላላለልኝ ነገር አጉል ከመልፋቱ ይሻለኝ ይሆናል አንገቴን መድፋቱ
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏