ብፁዕ ኾይ፦
እመቤታችን 'እንደ ቃልህ ይሁንልኝ' ያለችው ቃሏ የእርስዎም ቤዛ ነው።
"ከእናንተ መኖር ይልቅ የክርስቶስ ትንሣኤ ብዙ ማስረጃ አለው"
ክርስቶስ አልተነሣም ላሉ ሰዎች አንድ ሊቅ የተናገረው ቃል ነው።
የእመቤታችን ቤዛነትም እንዲሁ ነው። ከአቡኑ ማብራሪያና ዕውቀት ይልቅ ብዙ ማስረጃ አለው።ሌላውን ብዙ ጥቅስ ትተን
"ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ፤
እንደቃልህ ይሁንልኝ" ያለችው ቃል ብቻ በቂያችን ነው። የመጣው ለዐለም ኹሉ ቢኾንም የተወለደው ከእርሷ ነውና። 'ይሁንልኝ' ያለችው መልሷ የእርስዎም የእኛም ቤዛ ነው። ህየንተ (ምትክ) ማለት ነው።
ደግሞስ የድንግል ማርያም ቤዛነት ምኑ ይገርማል?
"ይኽ መስቀል ቤዛችን ነው" እያለ ቅዱስ ያሬድ ለመስቀሉ ዘምሮ የለምን?
"መስቀልከ ዕፀ ተነብዮ መስቀልከ ለሰይጣን ሞዖ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ።"
አኹን ቅዱስ ያሬድ ዕንጨቱን ቤዛ በማለት አምላክ አደረገ ብለን እናርመው?በፍጹም!
እንኳን እሱ፥ እኛ ስለ እመቤታችንም ኾነ ስለመስቀሉ ይኽን ስንል የፈጣሪን ቤዛነት ከፍጡራን ለይተን ዐውዱን ጠብቀን ነው።
ተሳስቻለሁ ይቅርታ ማለት ጴጥሮሳዊነት ነውና ቃልዎን እንደሚያርሙ ተስፋ አደርጋለኹ።
ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ