Orthodox Mezmur Channel


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


✞✞✞ Orthodox Mezmur Channel ✞✞✞

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቆየት ያሉ እና አዳዲስ መዝሙሮችን ያገኛሉ።
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All

ለማንኛውም ሀሳብ ፣ ጥቆማ ፣ አስተያየት
👇👇👇
@Orthodox_Mezmurs
@Orthodox_Mezmurs

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ
አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All




ቂርቆስ ለወዳጁ | ዘማሪ ዲያቆን ገዛኸኝ ኤርባ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All






አቡነ አረጋዊ ጻድቁ መነኩሴ | ዘማሪት ለምለም ከበደ

አቡነ አረጋዊ ጻድቁ መነኩሴ
በሃጢያት እንዳትሞት ሕያዊቷ ነፍሴ
ጻድቁ አማልደኝ በቅደመ ሥላሴ/2/
አዝ

ከእናት ከአባት ፍቅር አቡነ አረጋዊ
አምላክን መርጠሃል አቡነ አረጋዊ
መከራ መስቀል በእውነት ታግሰሀል
በእግዚአብሔር ቸርነት ከሞት ሰውሮሀል
አዝ

ምስጢረ መለኮት አቡነ አረጋዊ
በልብህ ቢሞላ አቡነ አረጋዊ
አረጋዊ ተባልክ ሳለህ ታናሽ ጨቅላ
ጸጋህ ትደርብን ትሁንልን ጥላ
አዝ

ከዳሞት ተራራ አቡነ አረጋዊ
ከማህሌት ከተማ አቡነ አረጋዊ
የጽዮን ዝማሬ ነፍስ ብትጠማ
በዘንዶ ተጉዘህ ሰማህ ያንን ዜማ
አዝ

የህግ መምህር አቡነ አረጋዊ
በረከት አድለን አቡነ አረጋዊ
ከድካም ወደ ሃይልህ በእምነት አሻግረን
ወደ ጌታ ደስታ በምልጃህ አቅርበን

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All








የጌታ ትንሣኤ | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ እና ዘማሪ ዲያቆን ሄኖክ ሞገስ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


የሕያዋን አምላክ | ዘማሪ ቀሲስ ወንድወሰን በቀለ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ተነስቷል በእውነት | ዘማሪ ዲያቆን ሳይዛና ጌታቸው እና ዘማሪ ዲያቆን እንዳለ ደረጀ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All




እንደተናገረ ተነስቷል | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም | ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ተነስቷል ጌታችን | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All




ትንሣኤከ ለእለ አመነ | ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️

  🕊 † ብርሃነ ትንሣኤ † 🕊

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

ዓለም በጨለማ ተውጣና የሰው ዘር በሙሉ በኃጢያት ቁራኝነት ተይዞ የዲያብሎስ ባሪያ በነበረበት ዘመን ብርሃናተ ዓለም ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ሞትን አጥፍቶ ብርሃንን ለገለጠበት ለትንሣኤው አድርሶናል ክብር ምስጋና ይገባዋል!!!

የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ የዘለዓለም አምላክ ወልድ ዋሕድ ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዕለት መግነዝ ፍቱልኝ ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በባሕርይ ኃይሉና ሥልጣኑ ተነስቷልና እንኳን ደስ አለን::

ከዚህ በኋላ ለ50 ቀናት እንዲህ እያልን ሰላምታ እንለዋወጣለን፦

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን !
¤ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን !
አሠሮ ለሰይጣን !
¤ አግዐዞ ለአዳም !
ሰላም !
¤ እምይእዜሰ!
ኮነ!
¤ ፍሥሐ ወሰላም !



Показано 20 последних публикаций.