#ብቻዬን_ተውከኝ
ከእለታት በአንድ ቀን እንዲህ ሆነ። አንድ ሰው በቤቱ ቁጭ ብሎ ያሳለፈውን ጊዜ ያስተውላል። በደስታው ጊዜ፣ በመሳቂያው ጊዜ፣ በእልልታው ሰዓት፣ ሁሉ በተመቻቸለት ጊዜ ዱካው አራት ሆኖ ያያል። በጣም ይገረማል በዚህ ሁሉ ጊዜ እግዚአብሔር አብሮኝ ነበር በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ። ሁለቱ ዱካ(ኮቴ) የራሱ እንደሆነ ሌሎች ሁለቱ ደግሞ የሚጠብቀው የእግዚአብሔር እንደሆነ ገብቶት እግዚአብሔር ሁሌ አብሮት ስላለ በመደነቅ እጅጉን አመሰገነው።
የችግሩ ጊዜ፣ የሀዘኑ ሰዓት፣ የህመሙ ጊዜ፣ የስቃዩ ጊዜ፣ የሰቆቃው ሰሞን፣ የለቆሱውን ዘመን፣ ሲመከት ግን ኮቴው ሁለት ብቻ ሆነ። በዚህ ምክንያት ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ እንዲህ አለው። እግዚአብሔር ሆይ አንተ በደስታዬ እና በድሎቴ ጊዜ አብረኸኝ ነበርክ። ነገር ግን የችግሬን ጊዜ ብቻዬን ተውከኝ ይኸው የሚታየኝ ዱካ ሁለት ነው በማለት እግዚአብሔርን መውቀስ ጀመረ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት። ልጄ ሆይ የውልህ የደስታህ ጊዜ አብሬህ መሆኔ ልክ ነው የችግርህ ጊዜ ችግርህን መሸከም አቅቶህ ነበር፣ ህመምህ ከአቅምህ በላይ ሆኖ ነበር፣ ብዙ ፈተናዎች ተደራርበውብህ ልትሸከመው ከምትችለው በላይ ሆኖብህ ስለነበር መራመድ አቅቶህ እኔ ተሸክሜህ ነበር። እና ያየኸው ሁለት ኮቴ የእኔ ነው። ልጄ እኔ ትቼህ አላውቅም ቢደክምህ እንኳን ተሸክሜህ ሁሉን አሻግርሃለሁ አለው።
እግዚአብሔር እኔ ጋር የለም ባላችሁበት በዛ ጊዜ እግዚአብሔር ግን እጅግ ቅርቃችሁ ሆኖ አተነፋፈሳችሁን እንኳን ይሰማል። ያለ እግዚአብሔር ያለፈ ዘመንና ዕለትም ጨርሶ የለም። በትጋት ተሻገርኩት ከማለት ይልቅ እግዚአብሔር አሻገረኝ ማለት እጅግ ማስተዋል ነው።
የሃሳብ ምንጭ:- አዲስ ህይወት መጽሐፍ
✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 መጋቢት 20 2016 ዓ.ም ተጻፈ
@orthodox_new_mezmur