ምንሊክ ለሮማው ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ለ ሌዎን ፲፫ ኛ የሰጡት ምላሽ
°°°°°
ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ዳግማዊ ምኒልክ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ
ይድረስ ወደተከበሩ የተቀደሱ የሮም ሊቀ ጳጳሳት ሌዎን ፲፫ ኛ
ሰላም ለርስዎ ይሁን።
የከበረው ያባትነትዎ ደብዳቤዎ ባቡነ መቃርዮስ እጅ ደረሰልኝ። በዚህም ደብዳቤዎ የቀድሞ መላላካችንን አሳምሮ የሚያስታውስ እግዚአብሔር ከኔ እጅ የጣላቸውን ስለኢጣልያምርኮኞች የቸርነት ሥራ እንድሰራ የሚያመለክት መሆኑን በጣም አየሁ። ደግሞም የከበረ ቅድስናዎ ከአቡነ መቃሮስ የበለጠ ነገሩን በጣም አስረድቶ አጣፍጦ ሀሳብዎን የሚናገር መላክ እንዳይቻልም አወቅን።
የክርስቲያን ሁሉ አባት የላከው እጅግ የሚያስደንቅ ደብዳቤዎን ባነበብኩ ጊዜ ልቤን መታው። ዳግመኛም የከበረውን የመልክተኛዎን የቃል ንግግር በሰማሁ ጊዜ ልቤ ቅድስናዎ በማክበር ለለመኑኝ ጉዳይ ለመፈጸም ጨክኖ ነበር። እኔ ሣልፈልገው በዚህ በከፋ ጦር ደማቸው ለፈሰሰ በከንቱ ላለቁት ወታደሮች እጅግ አለቀስሁ። ነገር ግን ቅድስናዎ የተመኙትን ለመፈጸም የኢጣልያ መንግሥት ያልታሰበው የዛሬ ሥራቸው የማያስፈጽመኝ ሆነ። ይህነንም ማለቴ የእርቅ ፈቃድና በደህና ለመላላክ ካሳዩኝ በኋላ ሥራቸው በጦርነት እንዳለኝ አድርገው ይሄዱ ዠመር።
አሁንም የሚገባኝ ንጉሥነቴና የሕዝብ አባትነቴ ይህን አውቀ በእጀ ያለውን የእርቅ መያዣ መልቀቅ የማይቻለኝ ሆነ። ቅድስናዎ ያሰበውን ሀሳብ ደስ ለማሰኘት የኔንም መልካሙን ሀሳብ ለመፈጸም ከለከለኝ። በክርስቲያንነቴና በንጉሥነቴ ልብ አውጥቼ አውርጄ ሳበቃ የፍቅሬን ምልክትና ብዙ ማፍቀሬን ሌላ ቀን አደርገዋለሁ ማለት ስለሆነብኝ ዛሬ ሳይሆንልኝ መቅረቱ እጅግ ያሳዝነኛል። እግዚአብሔር አደራ የሰጠኝ መንግሥቱን የሕዝቤን ነፃነት የምፈልግ ስለሆንሁ በክርስቲያኖች ሁሉ በማክበር የሚሰማውን የቅድስናዎ ድምጽ ለኛ ብለው እንደሚያሰሙልኝ ተስፋ አለኝ።
ይህ የሆነ እንደሆነ ከዘመዶቻቸውም ለተለዩ ምርኮኞች በቅርቡ ለመመለስ እንዲመቸን ማድረግዎ ነው። ነገር ግን ይህ ነገር እስኪጨረስ ድረስ ከኔ ዘንድ ያሉትን ምርኮኞች እንደ ክርስቲያን ሥራ ከዚህ ቀደም ጠብቄ በመልካም አድርጌ እንዳኖርኋቸው ይልቁንም ከእንግዴህ ወዲህ ስለርእዎ(ስለ እርስዎ) ፍቅር በጣሙን ጠብቄ በደህና አሣምሬ እንዳኖራቸው በዚህ አይጠርጥሩኝ። በመስከረም በ፳፪ ቀን ባዲስ፡ አበባከተማ ተጻፈ። በ፲፰፻፹፱ ዓመተ ምሕረት
via Jemal Abdulaziz