Let's Save Orthodoxy and humanity( ሰብእናንና ኦርቶዶክሳዊነትን እንታደግ)!!⁉️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ሰብእናንና የመንፈስ ልዕልናን ካዳበሩ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር በሰብእናና በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የሚፈጸምን(የተፈጸመን) ሥርዓታዊ፣መዋቅራዊ፣ሕጋዊ፣መናፍስታዊ፣ስነልቦናዊ ..ጥቃቶችንና አጥቂዎችን እንዲሁም ከጥቃት የመዳኛ መንገዶችን(መፍትሔ) የሚመለከትበት ቻናል ነው::

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ኦርቶዶክሳውያን እህቶቻችን አላችሁ አይደል

አቢሲኒያ ባንክ ያለ ዋስትና 55 ሚሊየን ብር የብድር አገልግሎት ለሴት ደንበኞቹ መስጠቱን ገለጸ

👉ባንኩ የዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ "እችላለው" የተሰኘ የሴቶች የተሰጥዖ ውድድር አዘጋጅቷል

የካቲት 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አቢሲኒያ ባንክ ለሴት ሥራ ፈጣሪ ደንበኞቹ ከ55 ሚሊየን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ያለምንም ማስያዣና ዋስትና መስጠቱን አስታውቋል።

የብድር አገልግሎቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለ125 ሴት ደንበኞች የተሰጠ መሆኑን የገለጹት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የደንበኞች ሂሳብ አገልግሎት ባለሙያ ሄለን ግርማ ናቸው።

ይህን መሰል አገልግሎት የሚሰጠው ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ሴቶችን ለማበረታት እና ለማገዝ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም የዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ "እችላለው" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ውድድር በመሳተፍ በአነስተኛ የወለድ መጠን እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በዚህ ዓመት ያለ ማስያዣ የብድር አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል።

በዚህም በውድድር ተሳትፈው አሸናፊ ለሚሆኑ 50 ሴቶች በአነስተኛ ወለድ ያለማስያዣ እስከ 500 ሺሕ ብር ድረስ የብድር አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንዲሁም ከብድር አገልግሎቱ በተጨማሪ ሴቶች መስራት በሚፈልጉት ዘርፍ ላይ የሥራ ፕሮፖዛል ቢያስገቡ፤ ሥራውን የተመለከተ ስልጠናዎች እንደሚመቻቹ አክለው ለአሐዱ ገልጸዋል።

የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ ለሴቶች የተዘጋጀው ውድድር ትናንት የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን፤ ማስረከቢያ ቀኑ መጋቢት 8 ቀን ይጠናቀቃል ተብሏል።

በባንኩ ለ4ተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የ"እችላለሁ" መርሐ ግብር፤ በሙዚቃ (በድምጽ)፣ በቲክቶክ ቪዲዮ እና በሥራ ፈጠራ ውድድሮች ላይ ተሰጥዖ ያላቸው እንስቶች እንዲሳተፉም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በቲክቶክ ቪዲዮ የተሰጥዖ ውድድር ባንኩ ለሴት ደንበኞቻችን ያዘጋጃቸውን 'አደይ' እና 'ዘሃራ' የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶችን በተለየ መንገድ የሚያስተዋወቅ መሆን ይኖርበታል ሲልም ባንኩ አስታውቋል፡፡

በፍርቱና ወልደአብ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ:: ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ::እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ:: የትዕቢትን ነገር አታስቡ:: ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ::"
ሮሜ. 12:15-16




Репост из: እምየ ተዋህዶ Emye Tewahedo
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ! 👑

የመላ ጥቁር ሕዝብ ድል የሆነውን የዓድዋን ጦርነት መርተው በድል ያጠናቀቁ መሆናቸው ብቻ አይደለም በዚህ ታሪካዊ ዕለት መወሳት ያለበት።

💥 ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አሁን የያዘችውን ቅርጽ ትይዝ ነበር ወይ?

💥 ለሀገራችን እንግዳ የሆኑ በርካታ ተቋማት እና ወሳኝ አገልግሎቶች 20 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ማግኘት ይቻል ነበር ወይ?

💥 ዘመናዊ አመራር እና አስተዳደር በአጭር ጊዜ እንዲዋሃደን ማድረግ ይቻል ነበር ወይ?

💥 20 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ባህልን እና ኃይማኖትን ሳይለቅ (without compromising religious and cultural values) አስተሳሰብን በዚያ ደረጃ መቀየር ይቻል ነበር ወይ?

💥 ከጦርነት እና ግጭት በላይ ዲፕሎማሲን የማስቀደም ልምድ ይኖረን ነበር ወይ?

💥 የሴቶችን ሚና ወሳኝነት እንቀበል/እንርረዳ ነበር ወይ?

💥 ዓለማቀፍ ጉዳዮች (የውጪ ጉዳይ)ን የተያዙበትን ጥበብ መማር ይቻል ነበር ወይ?

(ጨምሩበት)።

ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ን/ነ ዘ ኢትዮጵያ ዓለምን ከቀየሩ ጥቂት ክስተቶች አንዱ የሆነው የጥቁር ሕዝቦች ድል፣ የዓድዋ ድል ምልክት፣ የዘመናዊ አስተሳሰብ ፋና ወጊ እና ሀገር ወዳድ ምርጥ ''ጥቁር'' መሪ ነበሩ።

ክብር ለእርሳቸው እና በዓድዋ ጦርነት ተሳትፈውና ተሰውተው ነፃ ሀገር ላቆዩልን አባትና እናቶቻችን ይሁን! እንዲሁም ታሪኩን ብቻ ሰምቶ በመላው ዓለም በየዓመቱ በኩራት ለሚዘክረው ጥቁር ሕዝብ!

መልካም የዓድዋ ድል በዓል!

Hawlet Ahmed


እግዚአብሔርን መውደድ ሰውን መውደድ ነው።
እግዚአብሔርን መጥላትም ሰውን መጥላት ነው።
እግዚአብሔርን ማግኘት የሚቻለው በሰው በኩል ነው።
የወንጌል ተግባርም የምትፈጸመው ለሰው በምናደርገው መልካም ነገር ነው።
የሰው መድኃኒቱም ሰው ነው።

ለሰው የማያስብ ራስ ወዳድ የሆነ ሰው ግን የእግዚአብሔርን ሕግጋት የመፈጸም እድል የለውም።አንዱ ላንዱ የቀን እንደ ተራዳ የሌሊት እንደ ግድግዳ ሁኖ ሊያግዘው ግድ ነው።ያለዚያ ግን የቃል ዘመድ በገበያም አይገድ የተባለውን ይመስላል።

"በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ። ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም።ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ። በጨለማም ይመላለሳል የሚሄድበትንም አያውቅም ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።
"፩.ዮሐ.፪፥፱_፲፩ እንዲል።

ከምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት ገጽ


"ለሱ ያልተሠጠውን ልብስ ለመልበስ የሚጓጓ። በሌብነት የሚኖር ዓመፀኛ ቀማኛ ትግሉን በመጥፎ አካሄድ ያደረገ የሌላውን ሐብት የሚመኝ ቀረፅ የሚቀበል ክፋትን መሥራትና መናገር የሚያዘወትር መጥፎ ነገርን ለመሥራት የሚራቀቁትን ሰዎች የሚከተል ገንዘቡን በአራጣ የሚያበድር ከሰው ይህን አስፈፅምልሀለሁ እያለ ጉቦን የሚቀበል እነዚህን የመሳሰሉት ሁሉ እፀየፋቸዋለሁ።"
መጽሐፈ ቀሌምንጦስ 8:13




እኔ ሴት ነኝ ፤ ጦርነት አ ል ወ ድ ም : :  ሆ ኖ ም : ኢ ት ዮ ጵ ያ ን : የ ኢ ጣ ሊ ያ : ጥ ገ ኛ : የሚያደርግ ው ል : ከ መ ቀ በ ል : ጦ ር ነ ት ን : እ መ ር ጣ ለ ሁ : :

እቴጌ ጣይቱ ብጡል ኃ/ማርያም


Репост из: ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)
"ሰይፍ ዘጌዴዎን ኩይናት በእግዚአብሔር"

ሰልፍ የጌዴዎን ጦርነቱ በእግዚአብሔር ነው።
የምኒሊክ ተስፋው እግዚአብሔር ነው።


መምሬ "ካሳሁን እንግዳ" ይባላሉ በአድዋ ጦርነት ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት ይዘው በባዶ እግራቸው የዘመቱ አባታችን ናቸው።


ምንሊክ ለሮማው ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ለ ሌዎን ፲፫ ኛ የሰጡት ምላሽ

°°°°°

ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ዳግማዊ ምኒልክ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ

ይድረስ ወደተከበሩ የተቀደሱ የሮም ሊቀ ጳጳሳት ሌዎን ፲፫ ኛ

ሰላም ለርስዎ ይሁን።

የከበረው ያባትነትዎ ደብዳቤዎ ባቡነ መቃርዮስ እጅ ደረሰልኝ። በዚህም ደብዳቤዎ የቀድሞ መላላካችንን አሳምሮ የሚያስታውስ እግዚአብሔር ከኔ እጅ የጣላቸውን ስለኢጣልያምርኮኞች የቸርነት ሥራ እንድሰራ የሚያመለክት መሆኑን በጣም አየሁ። ደግሞም የከበረ ቅድስናዎ ከአቡነ መቃሮስ የበለጠ ነገሩን በጣም አስረድቶ አጣፍጦ ሀሳብዎን የሚናገር መላክ እንዳይቻልም አወቅን።

የክርስቲያን ሁሉ አባት የላከው እጅግ የሚያስደንቅ ደብዳቤዎን ባነበብኩ ጊዜ ልቤን መታው። ዳግመኛም የከበረውን የመልክተኛዎን የቃል ንግግር በሰማሁ ጊዜ ልቤ ቅድስናዎ በማክበር ለለመኑኝ ጉዳይ ለመፈጸም ጨክኖ ነበር። እኔ ሣልፈልገው በዚህ በከፋ ጦር ደማቸው ለፈሰሰ በከንቱ ላለቁት ወታደሮች እጅግ አለቀስሁ። ነገር ግን ቅድስናዎ የተመኙትን ለመፈጸም የኢጣልያ መንግሥት ያልታሰበው የዛሬ ሥራቸው የማያስፈጽመኝ ሆነ። ይህነንም ማለቴ የእርቅ ፈቃድና በደህና ለመላላክ ካሳዩኝ በኋላ ሥራቸው በጦርነት እንዳለኝ አድርገው ይሄዱ ዠመር።

አሁንም የሚገባኝ ንጉሥነቴና የሕዝብ አባትነቴ ይህን አውቀ በእጀ ያለውን የእርቅ መያዣ መልቀቅ የማይቻለኝ ሆነ። ቅድስናዎ ያሰበውን ሀሳብ ደስ ለማሰኘት የኔንም መልካሙን ሀሳብ ለመፈጸም ከለከለኝ። በክርስቲያንነቴና በንጉሥነቴ ልብ አውጥቼ አውርጄ ሳበቃ የፍቅሬን ምልክትና ብዙ ማፍቀሬን ሌላ ቀን አደርገዋለሁ ማለት ስለሆነብኝ ዛሬ ሳይሆንልኝ መቅረቱ እጅግ ያሳዝነኛል። እግዚአብሔር አደራ የሰጠኝ መንግሥቱን የሕዝቤን ነፃነት የምፈልግ ስለሆንሁ በክርስቲያኖች ሁሉ በማክበር የሚሰማውን የቅድስናዎ ድምጽ ለኛ ብለው እንደሚያሰሙልኝ ተስፋ አለኝ።

ይህ የሆነ እንደሆነ ከዘመዶቻቸውም ለተለዩ ምርኮኞች በቅርቡ ለመመለስ እንዲመቸን ማድረግዎ ነው። ነገር ግን ይህ ነገር እስኪጨረስ ድረስ ከኔ ዘንድ ያሉትን ምርኮኞች እንደ ክርስቲያን ሥራ ከዚህ ቀደም ጠብቄ በመልካም አድርጌ እንዳኖርኋቸው ይልቁንም ከእንግዴህ ወዲህ ስለርእዎ(ስለ እርስዎ) ፍቅር በጣሙን ጠብቄ በደህና አሣምሬ እንዳኖራቸው በዚህ አይጠርጥሩኝ። በመስከረም በ፳፪ ቀን ባዲስ፡ አበባከተማ ተጻፈ። በ፲፰፻፹፱ ዓመተ ምሕረት

via Jemal Abdulaziz


የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ሌኦን XIII ለምንሊክ የላኩት የተማጽኖ ደብዳቤ

«...በተባረከችይቱ ድንግል ወይም ከዚህ ዓለም በሚወዱት ስም የሚያቀርብልዎትን ልመና ይቀበሉና ...."

በጣም ኃያል ለሆኑት ምኒልክ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ
ሰላምና ገናናነት ለርስዎ ይሁን። ዛሬ አንድ ንጉሳዊ ልግስና እንዲያደርጉ የምክር ቃላችንን ክርስቲያናዊና ንጉሳዊ ለሆነው ልብዎ ለመላክ አሰብን። ይህ ድል ብዙ ምርኮኞች በእጅዎ ጥሎልዎታል። እነዚህምርኮዎች በወጣትነት ዘመን የኑሮኣቸው ተስፋ ባበበትና የብርሃን ጎህ በቀደደበት ሰዓት ካገራቸው ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው ይገኛሉ።

የነርሱ ምርኮ የግርማዊነትዎን ዝናና ገናናነት ምንም ሊያስፋፋው አይችልም። ይልቅ የምርኮ ዘመን ጊዜ በረዘመ መጠን በሺ የሚቆጠሩት ቤተሰቦቻቸው የመንፈስ ሀዘን እየበዛ ሄዷል። ከእየሱስ ክርስቶስ በተቀበልነው የተቀደሰ መልእክት እንደ ልጆቻችን እንወዳቸዋለን።

ስለዚህ ያንድ ልብ በቅድስት ስላሴ በተባረከችይቱ ድንግል ወይም ከዚህ ዓለም በሚወዱት ስም የሚያቀርብልዎትን ልመና ይቀበሉና ሳይዘገዩ ነፃነታቸውን ይስጡዋቸው። ኃያሉ ንጉሠ ነገስት ሆይ ይኽን የደግነት ስራ ባለመስራት እምቢታዎን ባለም ነገስታት ዐይን ፊት አይግለፁ። በወንድማማችነት እና በሰብአዊ ተግባር አንፃር ያለው የጦር መብትዎ ምንድን ነው የዚህን ብድር ርኀሩኅ አባት እግዚያብሔር በብዙ ይክስዎታል። ይህን ክብር ያላትን ደብዳቤ በመንግስትዎ ዜና መዋዕል ያስመዝግቧት።
እስከዚያው ለንጉሳዊ ቤተሰብ እግዚያብሔር በረከት እንዲያወርድ እንለምናለን።

ሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ
ግንቦት 11 ቀን 1896 ዓ.ም በ19ኛው ዘመነ ጵጵስና ተፃፈ»

ዋቢ፦ አፄ ምኒሊክና የኢትዮጵያ አንድነት


በሀዲያና ሥልጤ ሀገረ ስብከት105 ኢ-አማኒያን ተጠመቁ !

የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም

በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በዱና ወረዳ ቤተ ክህነት በጨፍሜራ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን 105 ኢ አማንያን ትምህርተ ሃይማኖት በመማር በዛሬው ዕለት ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።

መረጃው :-ብሕንሳ ሚዲያ


አድዋ፡ የመጨረሻው ውጊያ

« ከዚህ ቀጥሎ አጼ ምኒልክ ጦራቸውን ወደ አድዋ በመምራት የአድዋ ሸለቆ ከሚታይበት ከፍታ ላይ ሰፈሩ። ራስ መኮንን፣ ራስ መንገሻ እና ራስ ሚካኤልን ከመሃል ወራሪ፤ እራሳቸውን እና እቴጌን ከመካከል፣ ንጉሥ ተክለሃይማኖትን በስተቀኛቸው፣ ራስ አሉላን በስተግራ አደረጓቸው።

ጀነራል ባራቴሪ ከቅርብ ርቀት ላይ ቢሆንም የስንቅ እና ቁሳቁሶች እጥረት እየገጠመው ነበር። ስለዚህ በጥር ወር የምኒልክም ጦር ስንቅ እስኪያልቅ ጣልያኖች እንዲጠብቁ አዞ ነበር። ነገር ግን የጣልያን መንግሥት እርምጃ ውሰድ ዝምብለህ ከምትጠብቅ የሚል ትእዛዝ ስለላከ ሊተገብረው አልቻለም።

በየካቲት 23 ጥዋት ላይ ሊያጠቃ የነበረው ባራቴሪ ሦስት ሻለቃ ጦሮችን አሰለፈ። ጀነራል አልበርቶን በስተግራ፣ ጀነራል ዳቦርሚዳ በስተቀኝ እና ጀነራል አሪሞንዲ ከመካከል አድርጎ ደጀን ላይ ደግሞ ጀነራል ኢሌናን አስቀመጠ። አልበርቶን ራሱን ኪዳነምሕረት በምትባል ከፍታ ላይ አስቀምጦ የኢትዮጵያውያኑን እንቅስቃሴ ለመከታተል አስቦ ነበር።

ነገር ግን እሱ እንዳቀደው ሳይሆን ጀነራል አልበርቶን ዘው ብሎ ራስ አሉላ በሠፈሩበት አካባቢ ገባ። ሯጮች አጼ ምኒልክ ጋር ገስግሰው ጣልያን በጠዋት እንዳጠቃ ነገሯቸው። ዘበኞች ውጊያ ጀምረው ነበር። 25 ሺህ ሰዎችን ሲልኩላቸው አሪሞንዲን ከነበረበት ነቅለው እንዲሸሽ አደረጉት። 12 ሰዓት ላይ አልበርቶንን እና አስካሪዎቹን ወደ አሪሞንዲ ጦር ገፍተው አልበርቶንን ምርኮኛ ያዙት። የዳቦሪሚዳ ጦር እንኳን አልበርቶንን ሊያድን እራሱ ሳያስበው በራስ ሚካኤል ሰፈር ውስጥ ገብቶ ስለተከበበ ተደመሰሰ። የቀሩት የባራቴሪ ጦረኞች በንጉሥ ተክለሃይማኖት ተቆርጠው ተገደሉ። ቀን 6 ሰዓት ሲሆን በምኒልክ ሥር የዘመቱት የጦር መሪዎች በጦር ሜዳው ተሳትፈው ራሳቸውን አስመስክረዋል። የተረፉት ጣልያኖች ወደ ኤርትራ እግሬ አውጪኝ ሸሹ። እነሱም በኢትዮጵያ ገበሬዎች እየተጠቁ ኤርትራ የገቡት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

የአድዋ ጦርነት እንዲህ ተፈጸመ። ከ4 እስከ 5 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሞተው ወደ 8 ሺህ ያህል ቆስለዋል።  ጀነራል አልበርቶን እና 3ሺህ ጣልያናውያን ምርኮኛ ተወሰዱ። ከእነዚህ 200 የሚሆኑት በቁስሎቻቸው ምክንያት ሲሞቱ ወደ 800 አስካሪዎች ግራ እግራቸውን እና ቀኝ እጃቸውን ተቆረጡ። ከጠላት ጋር አብራችኋል በማለት። ጣልያኖች ወደ 7ሺህ ሰዎች ሲሞቱባቸው፣ 1500 ያህል ቆስሏል። 11 ሺህ ጠመንጃዎቻቸውም ተማርከዋል። »

ከፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት Ethiopian Warriorhood
ገጽ 234

ከጦቢያን በታሪክ ገጽ የተገኘ


"አባቶቻችን አንተን ተማመኑ:: ተማመኑ አንተም አዳንኻቸው" መዝ 21:4


አንኳን ለሰው ልጅ መኩሪያ ለሆነው የአድዋ ድል በሰላም አደረሳችሁ።

🔥🔥የካቲት 23, 1888 ዓ.ም


#ቅድስት
"ይህ መልእክት ለቅዱሳን ወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አምላችኋለሁ"
1.ተሰ 5፥27

የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ተብሎ የሚጠራ መሆኑ ይታወቃል!

ቅድስት በሚል ቅጽል የሚጠሩት፦
1. ሥላሴ
2. እመቤታችን
3. ጾም
4. ሰንበት
5. ቤተ ክርስቲያን
6. ነፍስ
7. መንፈስ ናቸው

ቅድስት ማለት 👉 ንጽሕት ክብርት ጽንእት ልዩ ማለት ነው።

ምሥጢሩ መለኮታዊ ቅድስናን የምንካፈልበት ጥግ የሚነገርበት ነው
በጣም ከፍተኛው የትምህርትም የሕይወትም ደረጃ ነው!

ልዕልና ነፍስ/የነፍስ ከፍታ የሚገኝበት
የመንፈስ ዕርገት/ንጥቀት/ምጥቀት/ርቀት
የሥጋ ንጽሕና የሚነገርበት ሳምንት ነው።

እግዚአብሔር ባህርያዊ ቅድስናውን በጸጋ እንዳካፈለን አውቀን ቸርነቱን የምናደንቅበት፤ ቸር መሆንን የምንለማመድበት ሳምንት ነው።

"እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ" ፣ ቆላ 3 ፥12።

ቅድስና ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መጣበቅ ማለት ነው
ይህም ሱታፌ ሥላሴ ወይም ኅብረተ ሥላሴ ወይም እግዚአብሔርን የመምሰል (Theosis) መደምደሚያ ነው።

የጸጋ አምላክነት/የጸጋ እግዚአብሔርነት ይገኝበታል!
ቅድስና በሂደት የሚገኝ እንደ እሳት እየተቀጣጠለ እንደ ነበልባል ወደ ሰማይ የሚያምዘገዝግ ሃይማኖታዊ ኃይል ነው!

የክርስትና ማብቂያው ይህን የቅድስና ሕይወት መለማመድ፣ማደግና በመጨረሻም ፍጹም በመሆን መዳን ነው።

"ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ"
1ኛ ጴጥ1፥15-16።

ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።
በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል"
2ኛ ጴጥ 1፥4&6

በተቀደሰ ሕይወት እንድንመላለስ የቅዱሳን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሐር ይርዳን!!!

አሜን

ሠናይ ሰንበት!

ከመጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው




ከ1878-1888ዓ.ም. ከዓድዋ በፊት የነበሩ 8ቱ አድዋዎችና የዓድዋ ሶሎዳ ውጊያ፤

1ኛ) ራስ አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ #ዶጋሊ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰበት፡፡

2ኛ) ደጃች ደበብ፤ #ሰገነይቲ ላይ የተደረገ ውጊያ

3ኛ) ደጃች ባሕታ ሀጐስና ወንድማቸው አዝማች ሰንጋል፤ ከጄነራል ሳጎናይቲና ከተከታዩ ታንቲ ጋር ያደረጉት ውጊያ፡፡ ቀጥሎም ደጃች ባሕታና ዘመዳቸው ባሻይ ምስጉን የተሰዉበት #የሐላይ መንደር ውጊያ፡፡

4ኛ) ራስ መንገሻ ዮሐንስ #በኰዓቲት ከጥር 13 -15 የተዋጉበት፤ ጦርነቱ የተራዘመና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት፤ የሟች ቊጥር በመበርከቱ አሸናፊና ተሸናፊው ሳይለይ፤ የራስ መንገሻ ጦር ወደ ሰነዓፌ የተበተነበት፡፡

5ኛ) የራስ መንገሻ ዮሐንስ የጦር አዝማቾች (እነ ተስፋይ ህንጣሎ አጋሜ፥ ወልደ ማርያም፥ ቀኛዝማች ኃይለማርያም ወምበርታ፥ ቀኛዝማች አብርሃ፥ ደጃች ረዳ አባ ጉብራ /የራስ አርአያ ልጅ/) መሪያችንን ራስ መንገሻን አናስነካም ብለው #በደብረ_አላ ላይ የተዋጉት ውጊያ፡፡

6ኛ) ልዑል ራስ መኰንን (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥና የሐረርጌ ገዥ /የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት/)፤ #አምባ_አላጌ ላይ ጣሊያንን እንደ ንብ ወረው ትልቅ ጀብድ የሠሩበትና ለአድዋውም ወኔ ቀስቃሽ ውጊያ፡፡

7ኛ) ልዑል ራስ መኰንን፤ መቀሌ #እንዳ_ኢየሱስ (ዛሬ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ግቢ የሚገኝበት) ላይ፤ ቀድሞ በቦታው ላይ ጠላት ሸምቆ ስለበረ ዙሪያውን ከበው ስንቅ በማሳጣት መሪው ማጆር ጋሊያኖ ማሩኝ ለጄነራሌ ለባራታሪ ሂጄ ዕርቅ ይሆናል አስማማለሁ፤ ብሎ በዕርቅ ያለቀበት፡፡ (ኋላ ግን ማጆር ጋሊያኖ ቃሉን በማጠፉና ጣሊያንን ለጦርነት በማነሳሳቱ የአድዋ ጦር ሁኗል፡፡)

8ኛ) ራስ ስብሐትና ደጃች ሐጐስ ተፈሪ (ቀድሞ ባንዳ ነበሩ) ማጆር ጋሊያኖ ለጄነራሉ ከማስማማት ይልቅ ጠብን በመምከሩና የጣሊያን ጦር በእንትጮ በኩል ከኢትዮጵያ ጋራ ሊዋጋ ሲገሰግስ የአካለ ጉዛይን ባላሃገር በማስተባበር #እንትጮ ላይ ደጀን ሁነው መክተው የተዋጉት ውጊያ፡፡

9ኛ)  #አድዋ #ሶሎዳ፡፡
ዓድዋ የሚለውን ስም የሠየሙት ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸው አባ ገሪማ ሲኾኑ፤ ዓድዋ ብዙ ተራሮችን የያዘች ሃገር ስትሆን፤ ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገው ከዓድዋ ተራሮች በግዙፉ #ሶሎዳ ተራራ ላይ ነው፡፡

"የኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት መነሻ"
ለአድዋ ጦርነት መነሻው፤ የአውሮፓ ኃያላን ሃገር ነን ብለው ራሳቸውን የሰየሙ አፍሪካን ሊቀራመቱ በተስማሙት መሠረት ጣሊያን ከሚስዮኖቿ አንዱና ተኩላ በሆነው አባ ማስያስ ሰላይነት ያጠኗትን ኢትዮጵያን ልትቀራመት መወሰኗ፡፡
መጀመሪያ በ1861ዓ.ም. እግሯን ወደ ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል አስገባች፤ በ17ዓመታት ቆይታ(እስከ 1878ዓ.ም.) ምጽዋን፣ የዳህላክ ደሴቶችንና የኤርትራን ቀይ ባሕር ያዘች፡፡ ምጽዋን በያዘች በ3ት ዓመታት ኤርትራን ያዘች፤ ኤርትራን በያዘች በ7 ዓመት መረብን ተሻግራ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመግባት ጦርነት ከፈተች፡፡ ራስ አሉላ አባነጋም ድባቅ መትቶ መለሳቸው፡፡

ይህ አልሆን ሲላቸው በተወካያቸው በአንቶኔሊ በሚያዝያ 25/1881ዓ.ም. በውጫሌ (ወሎ ቦሩ ሜዳ የምትገኝ) ላይ የተፈረመውን የውል ስምምንት አንቀጽ 17 በአማርኛና በጣሊያንኛ ቅጂው የተሳሰተ  (የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጭ ሃገራት ጋር የሚያደርገውንግንኙነት በኢጣልያ በኩል ማድረግ ይገባዋል!!፡፡›› በሚል ሰበብ ሌሎች ጠርነቶች ተቀሰቀሱ፡፡

በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።




Репост из: ዋቄ ገጽ
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#AbiyAhimed #Nazi-political the so clled "Oromuma" leader is the first leader in human history who is sleepless to create war, poverty and genocide of citizins based on their sub-identies.

In #Ethiopia the multifaceted strategy of genocide targets are: Orthodox christians and #Amhara Ethnollinguistics.
The worled is still turned blinedeye to these stark reality. Some of the diplomats in #addisababa ddis are even tryind to civerup the crimes.

Показано 20 последних публикаций.