መናፍቅ ነች አሉኝ!!
በሀጥያቴ ብዛት ከቤትህ ተነፍቄ
ከጉያህ ከእቅፍህ ከፊትህም ርቄ
አመት ቢቆጠርም ቢፈጠርም ዘመን
ቃል ግን ገብቶልኛል እኔን እንደሚያድን::
በድንግል ማህፀን በሆዷ ውስጥ አድሮ
ሊሽርልኝ ደዌ ስብራቴን ቀብሮ
መጣ ወደ በረት ከብቶች በሞሉበት
ህዝቡን ሁሉ ሊያድን ከሀሳብ ከጭንቀት
ቢጠመቅም ጥምቀት ቢፈተን ፈተና
እኔን ለማዳን ሁሉንም ቻለና
... ደግሞ ተሰቀለ እስኪከፋው ጥሙ
ኤሎሄ...ኤሎሄ አለ ቢበዛ ህመሙ ::
ነፍሱም አረፈች ፀሀይ ደበዘዘች
ጨረቃ አለቀሰች እንዴት አምላኬን እያለች
እኔን እና ጌታዬን የጋረደው ቆሞ
አልቻለም መቆየት ተቀደደ ፈጥኖ
መሬት ተናወጠች ቀኑም ጨለመ
በእየሱስ መሞት አማኝ ሁሉ ታመመ
ቢያስገቡት መቃብር በጨርቅም ጠቅልለው
በድንጋይ ቢያትሙት መዉጫውንም ፈጥነው
ሞትን ግን ድል ነሳ ይህም አልገደበው
ያኔ ብቻ አይደለም ዛሬም ቀኝ ተቀምጦ
እኔን ከሞት ከሲኦል አዉጥቶ
ዘዉትር ሲተጋልኝ ሆኖልኝ አማላጅ
በደሙ አስታርቆ አርጎኛል የ እግዜር ልጅ
ሀጥያቴ ቢሸት ቢገን እንደ ደም ፈልቶ
ያጠራ የለም ወይ ልክ እንደ ባዘቶ
ታዲያ....ዛሬ በየአደባባዩ
አማላጄ ጌታ ብል እሱን እዩ
አፌን አውጥቼ ብሰብክ በመድረክ
መካከለኛዬ እያልኩ ጉባኤ ባስመልክ
...ከሀዲ ናት አሉኝ
ጌታ ባወደስኩት መናፍቅ ተባልኩኝ
ምን አጠፋሁ እኔ የቱስ ነው ኩነኔ
ጌታ መማለዱ መቆሙ ስለኔ
ይልቅ ንገራቸው መናፍቅ ተብዬ
ጌታን አስከብሬደግሜ ብሰደብ አይደንቀኝምእኔ
መሲሁን አስቀድሜ እኔ በወረድኩኝ
ሌሎች ነፍሳት ግን መናፍቅ ነች አሉኝ
አሁንም እላለሁ አማላጄ ጌታ
ለኔ የተሰቃየው የሞተው ጎልጎታ
አደራ...አደራ... ጌታ ሆይ አደራ
መናፍቅነቱ ስድቡ አስጠልቶኝ
ከቤትህ ሸሽቼ ከጉያህም ርቄ ርዳኝ እንዳልገኝ
ግጥም እየፃፍኩኝ በቅኔ ሳስቀምጥ
መዝሙር ተቀብዬ በዜማ ብሰጥ
ትምህርት አዘጋጅቼ ወጥቼ ባስተማርኩ
ጌታን የካደች መናፍቅ ነች ተባልኩ!!!
ለአለም ለመቀር ከጌታ ለመታሰር
በደሙ በመዳን በቃሉ መፈወስ
ስሙን እየጠሩ እሱን ብቻ ማውደስ
ለጌትነቱ ዘላለም በፍቅሩ ለመኖር
መገኘቱን ናፍቀው ለክብሩ መዘከር
ናፈኩት ከጀልኩት ያንን ክብር
ሀሳቡ ሲገለጥ እውነቱ ሲፈካ
በፈራጁ ሚዛን ፍጡሩ ሲለካ
ተነጋሪ ተናጋሪ በተግባር ሲለካ
ያኔ እናወራለን ማን እንደ ነበር መናፍቅ
ከጌታ መንገድ ቀርቦ የሆነውን ሩቅ
ይፈርዳል ፈራጁ ሚዛን አያዛባም
ከሱ አይን ቁጥጥር ስር የወጣ የለም
ብዬ ብዘጋውም የጀመርኩትን ቅኔ
አስተውለህ አዉራ በል ንቃ ወገኔ
.....ዘመኑ ተገባዷል ሰከንዳት ቀርተዋል...
ልብህን አዘጋጅእንደተናገረውመሲሁ ይመጣል
React ❤️
✍ ዳግማዊት ፍቃዱ
✝✝✝✝✝✝✝
@revealjesus
በሀጥያቴ ብዛት ከቤትህ ተነፍቄ
ከጉያህ ከእቅፍህ ከፊትህም ርቄ
አመት ቢቆጠርም ቢፈጠርም ዘመን
ቃል ግን ገብቶልኛል እኔን እንደሚያድን::
በድንግል ማህፀን በሆዷ ውስጥ አድሮ
ሊሽርልኝ ደዌ ስብራቴን ቀብሮ
መጣ ወደ በረት ከብቶች በሞሉበት
ህዝቡን ሁሉ ሊያድን ከሀሳብ ከጭንቀት
ቢጠመቅም ጥምቀት ቢፈተን ፈተና
እኔን ለማዳን ሁሉንም ቻለና
... ደግሞ ተሰቀለ እስኪከፋው ጥሙ
ኤሎሄ...ኤሎሄ አለ ቢበዛ ህመሙ ::
ነፍሱም አረፈች ፀሀይ ደበዘዘች
ጨረቃ አለቀሰች እንዴት አምላኬን እያለች
እኔን እና ጌታዬን የጋረደው ቆሞ
አልቻለም መቆየት ተቀደደ ፈጥኖ
መሬት ተናወጠች ቀኑም ጨለመ
በእየሱስ መሞት አማኝ ሁሉ ታመመ
ቢያስገቡት መቃብር በጨርቅም ጠቅልለው
በድንጋይ ቢያትሙት መዉጫውንም ፈጥነው
ሞትን ግን ድል ነሳ ይህም አልገደበው
ያኔ ብቻ አይደለም ዛሬም ቀኝ ተቀምጦ
እኔን ከሞት ከሲኦል አዉጥቶ
ዘዉትር ሲተጋልኝ ሆኖልኝ አማላጅ
በደሙ አስታርቆ አርጎኛል የ እግዜር ልጅ
ሀጥያቴ ቢሸት ቢገን እንደ ደም ፈልቶ
ያጠራ የለም ወይ ልክ እንደ ባዘቶ
ታዲያ....ዛሬ በየአደባባዩ
አማላጄ ጌታ ብል እሱን እዩ
አፌን አውጥቼ ብሰብክ በመድረክ
መካከለኛዬ እያልኩ ጉባኤ ባስመልክ
...ከሀዲ ናት አሉኝ
ጌታ ባወደስኩት መናፍቅ ተባልኩኝ
ምን አጠፋሁ እኔ የቱስ ነው ኩነኔ
ጌታ መማለዱ መቆሙ ስለኔ
ይልቅ ንገራቸው መናፍቅ ተብዬ
ጌታን አስከብሬደግሜ ብሰደብ አይደንቀኝምእኔ
መሲሁን አስቀድሜ እኔ በወረድኩኝ
ሌሎች ነፍሳት ግን መናፍቅ ነች አሉኝ
አሁንም እላለሁ አማላጄ ጌታ
ለኔ የተሰቃየው የሞተው ጎልጎታ
አደራ...አደራ... ጌታ ሆይ አደራ
መናፍቅነቱ ስድቡ አስጠልቶኝ
ከቤትህ ሸሽቼ ከጉያህም ርቄ ርዳኝ እንዳልገኝ
ግጥም እየፃፍኩኝ በቅኔ ሳስቀምጥ
መዝሙር ተቀብዬ በዜማ ብሰጥ
ትምህርት አዘጋጅቼ ወጥቼ ባስተማርኩ
ጌታን የካደች መናፍቅ ነች ተባልኩ!!!
ለአለም ለመቀር ከጌታ ለመታሰር
በደሙ በመዳን በቃሉ መፈወስ
ስሙን እየጠሩ እሱን ብቻ ማውደስ
ለጌትነቱ ዘላለም በፍቅሩ ለመኖር
መገኘቱን ናፍቀው ለክብሩ መዘከር
ናፈኩት ከጀልኩት ያንን ክብር
ሀሳቡ ሲገለጥ እውነቱ ሲፈካ
በፈራጁ ሚዛን ፍጡሩ ሲለካ
ተነጋሪ ተናጋሪ በተግባር ሲለካ
ያኔ እናወራለን ማን እንደ ነበር መናፍቅ
ከጌታ መንገድ ቀርቦ የሆነውን ሩቅ
ይፈርዳል ፈራጁ ሚዛን አያዛባም
ከሱ አይን ቁጥጥር ስር የወጣ የለም
ብዬ ብዘጋውም የጀመርኩትን ቅኔ
አስተውለህ አዉራ በል ንቃ ወገኔ
.....ዘመኑ ተገባዷል ሰከንዳት ቀርተዋል...
ልብህን አዘጋጅእንደተናገረውመሲሁ ይመጣል
React ❤️
✍ ዳግማዊት ፍቃዱ
✝✝✝✝✝✝✝
@revealjesus