ጌታ ሆይ! አስተምረን! (ክፍል ሶስት)
“አስተማሪህ ከእንግዲህ አይሰወርብህም፤ ዐይኖችህም አስተማሪህን ያያሉ። ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል” - ኢሳ. 30:20 - 21
ያለፉት ትምህርቶች 1) “መጸለይን አስተምረን” እና፣ 2) “እድሜአችንን መቁጠር አስተምረን” ናቸው፡፡
ዛሬ ደግሞ ክፍል ሶስትን፣ ማለትም፣ “መንገድህን አስተምረኝ” የሚለውን እንመለከታለን፡፡
“አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ” - መዝ. 27፥11
ያለንበት የድህረ-ዘማነዊነት (post modernism) ዘመን፣ አንድ ነገር ላይ መድረሻው መንገድ ብዙ ነው በማለት ብዙዎችን የሚያስት ዘመን ነው፡፡ ጌታ ግን መንገዱ አንድ እና አንድ እንደሆነ፣ ያም መንገድ እሱ ጋር እንደሚገኝ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ” (ዮሐ. 14፡6) በማለት አስረግጦ ነግሮናል፡፡
ያለንበት መንገድ በርካታ ቀና የሚመስሉ አማራጭ መንገዶች ያሉበት ዘመን ነው፡፡ እነዚህን መንገዶች “ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያደርሳል” (ምሳ. 14:12) በማለት ቃሉ አመላክቶናል፡፡ ወደ እውነትና ወደ እውነት የሚወሰድውን መንገድ ግን የምገኘው ጌታ ጋር ነው፡፡
የስህተት መንገዶች ለጊዜው ከምናገኛቸው ጥቅሞች አንጻርና ውስጣችን ከተጠማው ጥማት አንጻር ስንመለከታቸው ትክክለኛ ሊመስሉን ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ቀና በሆነው መንገድና ቀና በሚመስለው መንገድ መካከል ግን ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ ይህንን ልዩነት ለማወቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ ነው ትክክለኛውን የእሱን መንገድ እንዲያስተምረን መጠየቅ የሚገባል፡፡
ጌታ ሆይ፣ ከእውነት መስመር ስቼ መጨረሻው ወደ ጥፋት የሚያደርሰውን መንገድ እንዳልከተል “መንገድህን አስተምረኝ”፡፡
Dr. Eyob Mamo