ሰማያዊ የንግግር ዘይቤ
“መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን”(1ቆሮ. 2፡13)፡፡
“ንግግር” በአስተሳሰብና በተግባር መካከል ልክ እንደሳንዲዊች ተጣብቆ የሚገኝ ነገር ነው፡፡ ንግግር አሳብን ሲከተል፣ በተራው ደግሞ ተግባርን ያስከትላል፡፡ ሰው ፈጠነም ዘገየም ሲያሰላስል የከረመውን በአንደበቱ ማውጣቱ አይቀርም፣ “በልብ ውስጥ የሞላውን አንደበት ይናገረዋልና” (ማቴ. 12፡34)፡፡
ይህ ሁኔታ እያደገ ሲሄድ ወደ ተግባር መለወጡ አይቀርም፡፡ በውስጡ የሞላው ሰማያዊው ከሆነ በአንደበቱ ያንኑ ሲናገር፣ በውስጡ ያለው ምድራዊው ከሆነ ደግሞ ምድራዊውን ይናገራል፡፡ ስለዚህ ንግግራችን የአስተሳሰባችን ነጸብራቅ ነው፡፡
ሰማያዊ የንግግር ዘይቤ ማለት ከምድራዊና ከተራ ንግግር የወጣና እንደ ቃሉ የሆነ ንግግር ማዳበር ማለት ነው፡፡ ይህ የንግግር ዘይቤ በሶስት ጎኑ ትኩረት ሊጠውና መስመር ውስጥ ሊገባ ይገባል፡፡
1. ለእግዚአብሔር የምናገረው
“በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ አልበደለም፤ በእግዚአብሔርም ላይ ክፉ አልተናገረም” (ኢዮ. 1:22)፡፡
አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎች እንደጠበቅናቸው አልሄድ ሲሉን ወይም ያልጠበቅናቸው ሁኔታዎች ሲጋፈጡን በጌታ ላይ የማጉረምረምና የእርሱን ባህሪያት የማይወክሉ ንግግሮች ከአንደበታችን እናወጣለን፡፡ ይህ ሁኔታ ለውስጥ ሰውነታችን ጥንካሬና በውጪ ላለው ምስክርነታችንን በእጅጉ የሚጎዳ ጉዳይ ነው፡፡ ለሰዎች ስለእግዚአብሔር የምንናገራቸውና ለእግዚአብሔር ለራሱ የምንናገራቸው ንግግሮች ወሳኝ ናቸው፡፡ “ስለዚህ ዘወትር የምስጋናን መሥዋዕት ይኸውም ለስሙ የሚመስክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በኢየሱስ አማካይነት ለእግዚአብሔር እናቅርብ” (ዕብ. 13፡15)፡፡
2. ለሰው የምናገረው
“ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ” (ኤፌ. 4፡29)፡፡
ይህ የብዙዎች ፈተና ነው፡፡ በየእለት ኑሯችን አንዳንድ ሰዎች የሚያሳዩትን ባህሪ ስንመለከትና ሁኔታው ሲነካን፣ ለሰዎቹ “የሚገባቸውን” ክፉ ቃላት ለማውጣት ይቃጣናል፡፡ ማስታወስ ግን ያለብን አንድ ቃላቶቹ ለሰዎቹ ተገባቸውም አልተገባቸውም፣ ከእኛ አንደበት ግን ሊወጡ የሚገባቸው ቃላት እንደሆኑ አምኖ መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ መላእክት እንኳን ከዲያቢሎስ ጋር ሲከራከሩ ጌታ ይገስጽህ ከማለት ካለፈ የስድብ ቃል ራሳቸውን ይጠብቁ ነበር፡፡
3. ለራሴ የምናገረው
“ብላቴና ነኝ አትበል” (ኤር. 1፡7)፡፡
ለራሳችንና በራሳችንን የምንናገራቸው ነገሮች በራሳችን ላይ ያለንን አመለካከት ጠቋሚ ናቸው፡፡ ጊዜያዊው ድካማችንና የተቃወሰው ስሜታችን ከሚነግረን ተቃራኒን በራሳችን ላይ መናገር አስፈላጊ እውነታ ነው፡፡ ምክንያቱም የጊዜው ሁኔታችን በክርስቶስ የተሰጠንን ስፍራ ስለማይወክል ማለት ነው፡፡ ስለዚህም፣ ሁኔታዬ የሚነገረኝን ሳይሆን ጌታ ያለኝንና ያሰበልኝን መናገር ታላቅ የብርታት ምንጭ ነው፡፡
የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ሰማያዊ የሕይወት ዘይቤ”
Dr. Eyob Mamo