🎉👌የዋጋ ማሻሻያ :- ውድ የራይድ ቤተሰብ - በቅድሚያ አብረውን ግዜዎን እና ጉልበትዎን ሰውተው ከተማችንን ለማገልገል ፍቃደኛ ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን:: ስራችን የጋራ እንደመሆኑ መጠን ደንበኞቻችንን በማያሸሽ እና የመክፈል አቅማቸውን በማይፈታተን መልኩ Baseline ሂሳባችንን ቀርፀን ለአባላት አዋጭ ማድረግ እንዳለብን ከሰበሰብነው የሃሳብ መስጫ ቅፆ Survey ተረድተናል:: በዚህም መሰረት ድርጅታችን ለሚቀጥሉት 9 ወራት የዋጋ ተመን ማስተካከያ ለማድረግ Pricing Strategy ነድፎ ከሰኞ OCT 7 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ እየገለፅን- እርስዎም ደንበኛን በማግባባት እና በመያዝ የበኩልዎን እንዲወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን:: በመጀመርያው ረድፍ ጭማሪ (ወር 1) መነሻችንን ከ100 ብር ወደ 130 ብር ከፍ የምናደርግ ሲሆን- Duration ክፍያን ደግሞ በደቂቃ ከ2.50 ወደ 3ብር ከፍ የምናደርግ ይሆናል:: በመቀጠልም ለተከታታይ 8 ወራት በየወሩ ገብያን ያማከለ ዝቅተኛ ጭማሪ ቀስ በቀስ የምናደርግ ይሆናል:: ከራይድ ጋር ወደፊት!