ሳይኮሎጂስቶች እንደሚሉት ሐዘን (grief ) አምስት ደረጃዎች አሉት ። የመጀመሪያው ደረጃ denial ይባላል ። የተፈጠረውን ነገር አልተፈጠረም ብለን የምንክድበት ደረጃ ነው ። ሁለተኛው ደረጃ anger ይባላል ። "ለምን ? ምን በደልኩ ?" እያልን የምንተክዝበት እና ከመሬት ተነስተን በሁሉም ነገር የምንነጫነጭበት ደረጃ ነው ። ሶስተኛው ደረጃ bargaining ይባላል ። እስከዛሬ ከሸሸነው ነገር ጋር ፊትለፊት የምንጋፈጥበት ደረጃ ነው ። አራተኛው ደረጃ depression ይባላል ። የተፈጠረውን ነገር አምነን የምናዝንበትና የምናለቅስበት ደረጃ ነው ። አምስተኛውና የመጨረሻው ደረጃ Acceptance ይባላል ። እዚህኛው ደረጃ ላይ ሐዘኑን ሙሉ ለሙሉ ተቀብለን እና "ለበጎ ነው" በማለት ተጽናንተን ወደፊት የምንጓዝበት ደረጃ ነው ።
ብቻ ምን ልል ነው እነዚህን ደረጃዎች ሳይኮሎጂስቱና ባለቅኔው በውቀቱ ስዩም በሚያምር አማርኛና አገላለጽ በውስን መስመር እንዴት እንደገለጻቸው ተመልከቱ ለማለት ነው
አዎ !
ለጊዜውም ቢሆን ፤ ግፍ ያደነዝዛል (denial)
በደል ያስተክዛል (anger)
ጊዜም ጠብን ሽሮ ፤ ወደፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል (bargaining )
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፤ ሚስቱን ያስረግዛል ። (depression & acceptance)
Cc habtamu hadra
@Samuelalemuu
ብቻ ምን ልል ነው እነዚህን ደረጃዎች ሳይኮሎጂስቱና ባለቅኔው በውቀቱ ስዩም በሚያምር አማርኛና አገላለጽ በውስን መስመር እንዴት እንደገለጻቸው ተመልከቱ ለማለት ነው
አዎ !
ለጊዜውም ቢሆን ፤ ግፍ ያደነዝዛል (denial)
በደል ያስተክዛል (anger)
ጊዜም ጠብን ሽሮ ፤ ወደፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል (bargaining )
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፤ ሚስቱን ያስረግዛል ። (depression & acceptance)
Cc habtamu hadra
@Samuelalemuu