በዋሽንግተን ግዛት የአሜሪካ ልዩ ኃይል ወታደሮች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዙ
የአሜሪካዋ ዋሽንግተን ግዛት ገዥ አርብ እለት እንደተናገሩት ከምርጫ 2024 ጋር ተያይዞ ሁከት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል መረጃ እና ስጋት መኖሩን ተከትሎ የተወሰኑ 'የናሽናል ጋርድ' ወይም ብሔራዊ ዘብ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ አድርገዋል።
በህዝብ አስተያየት መሰረት የዲሞክራቷ እጩ ካማላ ሀሪስ የሪፐብሊካኑን እጩ ድናልድ ትራምፕን በቀላሉ ያሸነፉበታል የተባለው ይህ ግዛት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የምርጫ ኮሮጆ ከተቃጠሉባቸው መካከል አንዱ ነው።
"ከምርጫ 2024 ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ጥቅል ወይም የተለዩ መረጃዎችን እና ስጋቶችን በተመለከተ፣ ምላሽ ለመስጠት በደንብ መዘጋጀታችንን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ" ሲሉ ገዥው ጄይ ኢንስሌ አርብ እለት በጽረ-ገጻቸው ላይ በታተመ ጽሁፍ መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።