ለሠራተኞቻቸው በነጻ ምግብ የሚያቀርቡት ኩባንያዎች
ከእነዚህ ድርጅቶች መካከል በዓለማችን የሚገኙ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ይጠቀሳሉ፡፡
ኩባንያዎቹ ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች መካከል የነፃ ምገባ፣ ማረፊያ፣ መዝናኛና ሌሎች አገልግሎቶች ይገኙበታል፡፡
ከእነዚህ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መካከልም ፌስቡክ፣ ጉግል፣ አፕል፣ ኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) እና ማይክሮሶፍት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ፌስቡክ
የፌስቡክ ካፊቴሪያዎች ለሠራተኞቻቸው እና ለእንግዶቻቸው የአሜሪካና የእስያ የምግብ ዓይነቶችን በነፃ ያቀርባሉ፡፡
ጉግል
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል 18 ካፊቴሪያዎች ሲኖሩት፥ ለሠራተኞቹ የተለያዩ የምግብና መጠጦች አማረጮችን መሰረት በማድረግ በነፃ በማቅረብ ይታወቃል፡፡
አፕል
የአፕል ካፊቴሪያዎች ለሠራተኞች እና ለእንግዶች ሙሉ በሙሉ ነፃ የምግብ አገልግሎት ያቀርባሉ፡፡ በዚህም የስፓኒሽ፣ የሜክሲኮ፣ የጣሊያን፣ የጃፓን እና ፈረንሣይ ምግቦችን እንደየ ሰዎቹ ፍላጎት ያዘጋጃሉ፡፡
ኤክስ (የቀድሞው ትዊተር)
የኤክስ ካፊቴሪያ ለኩባንያው ሠራተኞች የተለያዩ ምግቦችንና መጠጦችን በነፃ ይሰጣል፡፡
ማይክሮሶፍት
የማይክሮሶፍት ካፊቴሪያ ለሠራተኞቹ ምግቦችን በዝቅተኛ ዋጋ እንደሚያቀርብ ክሎክ ኢት ዘግቧል፡፡
ኩባንያዎቹ እነዚህን አማራጮች በመጠቀም ሠራተኞቻቸውን እየደጎሙ ሥራቸውን በይበልጥ ለማሳለጥ እየተገበሩት ያለው የነጻ አገልግሎት ውጤታማ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡