በቄለም ወለጋ ዞን የሸኔ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው እየገቡ መሆኑ ተገለጸ‼️
በቄለም ወለጋ ዞን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሸኔ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በደንቢ ዶሎ የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች የዞኑ አመራሮች በተገኙበት ትጥቃቸውን ማስረከባቸው ተገለጸ።
የቄለም ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳራ ገመቹ ጉርሜሳ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል እና የሠላምን አማራጭ ተቀብለው ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸው የሰላምን አስፈላጊነት መገንዘባቸው መረጋገጫ ነውና እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች በበኩላቸው ይህን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የመጡ የሸኔ ታጣቂዎች ሠላም ለኢትዮጵያ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተረድተው የመጡ በመሆናቸው ቀጣይ በሠላምና በልማት ሥራ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ተስፋ እናደርጋለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።