በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባቀረበው የሠላም ጥሪ መሠረት የኦነግ ታጣቂ ኃይል አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በስፋት እየገቡ መሆኑ ይታወቃል።
የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማጓጓዝ ስራ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል።
በዚህ መሀል ታጣቂዎቹ አዲስ አበባ ከተማን አቋርጠው ወደ ስልጠና ማዕከላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እየጨፈሩና የደስታ ስሜት እያሰሙ ሲንቀሳቀሱ የተኩስ ድምጽ በማሰማታቸው በከተማው ነዋሪ ህዝብ ላይ ድንጋጤና መረበሽ ሊፈጠር መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።
ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ የጠየቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስታውቋል።