የዓለማችን ረዥሙ ሾፌር አልባ የባቡር የጉዞ መስመር ስራ ጀመረ‼️
በሳዑዲ አረቢያ መዲና ሪያድ በቅርቡ ወደስራ የገባውና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚታገዘው ሾፌር አልባ የመንገደኞች የባቡር አገልግሎት ፈጣን፣ ወጪ ቆጣቢ እንዲሁም ደህንነቱ አስተማማኝ ነዉ ተብሎለታል፡፡
የትራፊክ ምልክቶችን መረዳት፣ የባቡሩን ፍጥነት መቆጣጠር፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ አስቀድሞ ማሳወቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ለባቡሩ ከሚሰጠዉ ጥቅም ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተሳፋሪዎችን የጉዞ ሁኔታ መከታተል ያስችላል፡፡
አገልግሎቱ በቀን 3.6 ሚሊዮን መንገደኞችን በሙሉ አቅሙ በስድስት የጉዞ መስመሮች የማጓጓዝ አቅም እንዳለው ገልፍ ቢዝነስ ዘግቧል፡፡ በዚህም ዘላቂ የትራንስፖርት አማራጭ በማቅረብ በሪያድ ያለውን የካርቦን ልቀት ለመቀነስ እና የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡
በ23 ቢሊዮን ዶላር በጀት ወደስራ የገባው የባቡር አገልግሎት 176 ኪ.ሜ ገደማ የሚሸፍን ሲሆን የሀገሪቱን የትራንስፖርት ስርዓት አዲስ መልክ እንደሚሰጠዉ ይጠበቃል፡፡