❗️ "በምርጫ ቦርድ ብንሰረዝም ባንሰርዝም ፋይዳ የለውም" - ሕወሓት ❗️
ሕወሓት በመግለጫው "በተደጋጋሚ እንደተገለጸው ሕወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ ከአሸባሪነት ተሰርዞ ወደ ሕጋዊ ማንነቱ እንዲመለስ እንጂ እንደ አዲስ ፓርቲ ለመመዝገብ ጠይቀን አናውቅም" ብሏል።
ሕወሓት አክሎም "የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያልጠየቀውን፣ ያልተቀበለውን እና በሕግ ላይ ያልተመሰረተ ዕውቅና ቢሰርዝም ባይሰርዝም ህጋዊ ፋይዳ የለውም" ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በፍትሕ ሚኒስቴር ተጻፈ የተባለው ደብዳቤም ያልተጠየቀ እና ሕወሓት የማያውቀው እንዲሁም በይዘቱ በፍጹም የማይስማማበት ስለመሆኑ መግለጫው ያትታል።
በዚህ ያላበቃው ሕወሓት የፌደራል መንግሥት የፕሪቶሪያን መንፈስ እና የጽሑፍ ሥምምነት በትክክል በመተግበር የትግራይን ህዝብ ችግር ለማቃለል ግዳጁን መወጣት አልቻለም ሲል ወቅሷል።
በተጨማሪም "የፕሪቶሪያ ሥምምነት በአስቸኳይ እንዲተገበር እንጠይቃለን"ሲል በመግለጫው አስታውቋል።
(Arts tv)