ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ ይጠበቅባቸዋል ተባለ
ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉም ተነግሯል
የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ አክስዮን ማህበር ከዛሬ የካቲት 24 ጀምሮ መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ከፍተኛ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ወይዘሮ እስራኤል ወልደመስቀል ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የመንገደኞችን እንግልት ለመቀነስና ለጋራ ደህንነት መንገደኞች ከዛሬ ጀምሮ የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት በመቁረጥ አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ተደርጓል።
ማህበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ዲጂታላይዝድ ማድረጉን የገለጹት ባለሙያዋ፤ ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉም ተናግረዋል።
ይህንንም ለደንበኞች የማሳወቅ ሥራው ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ሲሰራ እንደነበርና ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር መታወቂያውን እንዲያገኙት እየተደረገ እንደነበር አስታውሰዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ ተግባራዊነቱ ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ብቻ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ተጠቃሚዎች ፓስፖርታቸውን በመጠቀም ትኬት ማግኘት እንደሚችሉ ወይዘሮ እስራኤል ገልጸዋል።
በኦንላይን ትኬት የመቁረጥ አገልግሎት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል።