⚡️በየቀኑ 2 ሺህ ሰዎች በኤችአይቪ
በዩኤስኤይድ መዘጋት የተነሳ በየቀኑ 2 ሺህ ሰዎች በኤችአይቪ ሊያዙ እንደሚችሉ ተመድ ገለፀ፡፡
የተመድ የኤድስ ኤጀንሲ ዛሬ እንደገለፀው ዩኤስኤይድ በመዘጋቱ የተነሳ ከኤችአይቪ ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ይሰጥ የነበረው አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳደረውም በዚህ ላይ ነው፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዊኒ ባኒማ ሲናገሩ ‹‹የአሜሪካ መንግስት በድንገት ድጋፉን በማቋረጡ በርካታ ክሊኒኮች ከመዘጋታቸውም በላይ በሺህ የሚቆጠሩ የጤና አገልግሎት ሰጪዎችም ተቀንሰዋል፡፡
ይህ ደግሞ አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እንዲጨምር አድርጎታል›› ካሉ በኋላ በየቀኑ ሁለት ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ የሚል ግምት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡
የዩኤስኤይድ እርዳታ ተመልሶ ካልቀረበ ወይንም ሌላ መንገድ ካልተፈለገ በሚቀጥሉት አራት አመታት ስድስት ሚሊዮን ከኤችአይቪ ጋር የተገናኘ ሞት ሊከሰት እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል፡፡
@seledadotio