Regulation-No.-557-2016-compressed.pdf
ይህንን ማንበብና ለወዳጅ ማጋራት ተገቢ ነው።
ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፦
👉ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።
👉አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።
👉የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።
👉 የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።
👉 ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።
👉የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ
👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።
👉 ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
👉 የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።
👉አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
- 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።
👉በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።
👉 የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።
👉ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
👉የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
👉 የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
👉ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
👉 የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
👉ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
👉ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።
👉 የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።
👉 የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
👉ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
👉 ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
👉 መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።
(Tikvah ethiopia)
@sheger_press