#ትጥቁንና ልብሱን አውጥቶ በንጉሱ ፊት ወረወረው
ሮማዊ ነው፤ ቤተሰቦቹ አረማውያን ሲሆኑ ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የተመለሱ ናቸው፡፡ አባቱ ፊታቸው የውሻ የሆነ፣ የአውሬነት ጸባይ ያላቸው በእግዚአብሔር ኃይል የሚታዘዙት ሁለት አገልጋዮች ነበሩት፡፡ በመርዶሳውያን ሀገር ተማርኮ የሔደው አባቱ ጸጋ እግዚአብሔር በዝቶለት በዚያ ሹመት አጊቷል፡፡ አባትና እናቱ ሲያርፉም ልጃቸው ስልጣኑን ተረክቧል፡፡ በክርስትናው ዓለም በዓለም አቀፍ ደረጃ ታሪካቸው ከሚነገርላቸው ሰማዕታት አንዱ በሀገራችን በኢትዮጵያም በአማላጅነቱ የሚታወቀው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ፡፡ መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው። በሁለተኛ ትርጉሙ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው። በሀገራችን በኢትዮጵያም በበርካቶች ዘንድ በፈጣን ተራዲኢነቱ ይታወቃል፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፣ ቅዱስ መርቆሬዎስ የአባቱን ስልጣን ወርሶ በንጉስ ዳኪዮስ ስር በመርዶሳውያን አገር ላይ ተሾመ፡፡ መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፤ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፤ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በጦሩ መካከል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን “እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ” አለው፤ ከዚያም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና “ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው” አለው፡፡
ጦርነቱ በንጉሱ ዳኪዮስ ወገን አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ በድሉ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡ ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት “ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት ረሳህ” አለው፡፡
ንጉሥ ዳኬዎስ ግን ከጦርነቱም በኋላ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ በዚህ ያዘነው ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በበዓሉ ላይ አልተገኘም፡፡ ንጉሡ ይህንን ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣውና “ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?” አለው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ “ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፤ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም” አለው፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በክርስትናው የተፈተነው፡፡
ንጉሡ አብሮት በጣኦት አምልኮው ስላልተሳተፈ በልዩ ልዩ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የሀገሩ ሰዎች እንዳይነሡበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡
በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ በንጉሥ ዳኬዎስ ትዕዛዝ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፤ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፤ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡
እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡ በየወሩ በ25 ቀንም መታሰቢያው ነው፡፡ ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ዓለም የምትሰጣቸውን ምቾት ትተው ክርስቶስን ብለው ወጥተዋል፡፡
ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444