በአዲስአበባ ተገቢ ባልሆነ ቦታ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን ለማስቀረት መመሪያ እየተዘጋጀ ነዉ ተባለ
በየመንገዱ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን መቀነስ ተችሏልም ተብሏል
በአዲስ አበባ ተገቢ ባልሆኑ ቦታዎች ላይ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን መቀነስ እንደተቻለ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው በወቅቱ እንደተናገሩት በሜክሲኮና በመገናኛ አደባባዮች የሚደረጉ ስብከቶች ላይ በተከታታይ የግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም መታረም የሚገባቸውን በማረም የችግሩን መጠን ከነበረበት መቀነስ ተችሏል።
የአደባባይ ስብከቶችን በሚገባቸው ሐይማኖታዊ ቦታዎች እንዲደረጉ ከሐይማኖት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሐይማኖታዊ ነጻነትን በማይጋፋ እና ህገ ወጥነትን መከላከል በሚያስችል መልኩ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
እንደሀገር ተገቢ ባልሆነ ቦታ ላይ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ስብከቶችን ለማስተካከል እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመመሪያ ማውጣቱ ሂደት ቢሮውን ጨምሮ የሐይማኖት፣ የተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት እንደሚገኙበት አስረድተዋል።
#EPA
@sheger_press